በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የግብርና ኮሌጅ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረዉን አለም አቀፍ  የፀረ-ሙስና ቀን “ሙስናን መታገል በተግባር” በሚል መሪ ቃል ታህሳስ 4 ቀን 2015 ዓ.ም አክብሯል።

በግብርና ኮሌጅ የስነ-ምግባር መከታተያና ፀረ- ሙስና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ዮሐንስ ሣህሉ  በመክፈቻ ንግግራቸው በአንድ ሀገር ህዝቦች ሰርተው የሚከብሩት፣ ዲሞክራሲ የሚዳብረው፣ እድገትና ብልፅግና የሚረጋገጠው ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት ሙያ የበኩሉን ሲወጣና ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን መከላከል ሲችል መሆኑን አውስተው ሙስና፣ ብልሹ አሰራርና ኢ-ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል በአንድ ሀገር ካለ ጥቂቶች በልፅገው ብዙሃኖችን ለድህነት እንዲዳረጉ መገደዳቸው የማይቀር በመሆኑ የሚፈለገው ሰላም፣ ዕድገት እና ለውጥ እንደማይመጣ ተናግረዋል፡፡ 

አክለዉም ሙስና ከግለሰብ አንስቶ በሀገር ደረጃ ከባድ ጉዳት እንደሚያደርስ ገልፀዉ ይህንን አፀያፊ ተግባር ለማስተካከል ሁላችንም በንደፈ ሃሳብ ከማወቅ በዘለለ እኛስ ምን እያደረግን ነው ብለን እራሳችንን በመፈተሽ በተግባር ልንታገለዉ ይገባል በማለት ሁላችንንም  የተሰጠንን ተልዕኮ ለመወጣት በተሰማራንበት ሙያ  ጊዜያችንን፣ ሀብታችንን እና እዉቀታችንን ለታሰበለት ዓላማ በማዋል ሙስናንና ብልሹ አሰራርን የሚፀየፍ ብቁ ዜጋ በየዘርፋችን ልናፈራ ይገባናል ብለዋል።

በዕለቱም  ተሳታፊዎች ዕለቱን አስቦ ከማክበር በዘለለ ሙስናን ለመታገል ከእኛስ ምን ይጠበቃል በማለት ውይይት ያደረጉ ሲሆን ዕለቱም “ሙስናን መታገል በተግባር” በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

 “ሴትን አከብራለሁ፤ ጥቃቷን እከላከላለሁ” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ወይም ነጭ ሪቫን ቀን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር አዘጋጅነት በደማቅ ሁኔታ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተከብሯል ፡፡

Page 40 of 100

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et