ለድህረ ምረቃ ተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ

የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ለድህረ ምረቃ ተማሪዎች ስልጠና ሰጠ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ለድህረ ምረቃ ተማሪዎች መረጃን ለመተንተን የሚረዱ ሶስት ሶፍትዌሮች ላይ ታህሳስ 7 ቀን 2015 ዓ.ም ስልጠና ሰጥቷል።

የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዙፋን በደዊ ኮሌጁ በእስታስቲክስ ት/ክፍል በኩል ለሁለተኛና ለሶስተኛ ድግሪ ተማሪዎች በመመረቂያቸዉ ወቅት ለሚሰሩት ምርምሮች መረጃን ለመተንተን የሚያስችሏቸዉን የSTATA, R እና SPSS ሶፍትዌሮችን እያሰለጠነ እንደሆነ ገልፀዉ  የዚህ መሰሉ ስልጠና በዚህ ዓመት ለሁለተኛ ጊዜ እየተሰጠ ሲሆን ለመምህራኖችም ጠቃሚ እንደሆነ ተናግረዋል።

የኮሌጁ ምክትል አካዳሚክ ዲን ዶ/ር ይፋት ደንባርጋ የዚህ መሰሉ ስልጠና ተማሪዎች የሚሰሩትን ጥናት ለማደራጀትና መረጃዎችን ለመተንተን የሚረዳ በመሆኑ ጥራት ያላቸዉ ሳይንሳዊ ምርምሮችን ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዉን ተልዕኮ ለማሳካት ጉልህ ሚና ይኖረዋል ያሉ ሲሆን ስልጠናዉን ለመዉሰድ በርካታ ፍላጎት ያላቸዉ ተማሪዎች በመኖራቸዉ ስልጠናዉ ቀጣይነት እንዳለዉም ተናግረዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et