የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሄደ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2016 በጀት ዓመት አጠቃላይ ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2017 የሥራ ዕቅድ ግምገማና ውይይት መድረክ በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እየተካሄደ ነው::

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በራሶ መድረኩን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው በ2016 ዓ.ም የነበረው የስራ አፈጻጸም በብዙ ተደራራቢ ሥራዎችና ሃገራዊ ግዴታዎች መካከል አልፎ በርካታ አመርቂ ውጤቶች የተመዘገቡበት መሆኑን አንስተዋል::

ፕሬዚደንቱ በሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የመደበኛ ተማሪዎች መካከል ከ91% በላይ የሚሆኑት ፈተናውን ማለፋቸውንና ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ በስተቀር ሌሎቹ ኮሌጆች ሁሉ በትምህርት ካላንደሩ ላይ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈጠረውን መዛባት ማስተካከላቸውን እንደማሳያ አቅርበዋል። ክፍተት ከተስተዋለባቸው ዘርፎች መካከል በተከታታይ ትምህርት መስክ በቂ ውጤት አለመመዝገቡ እንዲሁም ከበጀት እጥረት ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ክፍተቶችን መንስኤ በመለየት በቀጣይ በሚኖረው እቅድ ላይ የመፍትሔ አቅጣጫ ሊቀመጥ እንደሚገባም ዶ/ር አያኖ ተናግረዋል።

በመጀመርያው ቀን ውሎ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚደንት: የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚደንት: እና የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚደንት የየፅህፈት ቤታቸውን ዓመታዊ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ጥያቄ: አስተያየትና ግብረመልስ ተሰጥቷቸዋል::

በተጨማሪም የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለጉባኤው ተሳታፊዎች የደም ልገሳ እንዲያደርጉ ያመቻቸ ሲሆን "በጎነት ለጤናችን" በሚል መርህ በጤና ሚኒስቴር የሚመራውን ሃገራዊ ንቅናቄ ተከትሎ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ነፃ ምርመራ ለተሳታፊዎች አቅርቧል:: በዚህም የዓይን ምርመራ: የጥርስ እጥበት: የስኳርና ደም ግፊት ምርመራዎች ፈቃደኛ ለሆኑ አባላት ሰጥተዋል::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et