ሙስናን መታገል በተግባር

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስናን መታገል በተግባር በሚል መሪ ቃል የፀረ ሙስና ቀን ተከበረ፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ  በስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት “ሙስናን መታገል በተግባር” በሚል መሪ ቃል ታህሳስ 11 ቀን 2015 ዓ.ም የፀረ ሙስና ቀን ተከብሯል፡፡

የምርምርና ቴ/ሽ/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዮስ ሙስናና የስነ ምግባር ችግር ለአለምችን እና ለሰው ልጆች ፈተና ሆኖ የቆየ ሲሆን በተለይ በአፍሪካ በሚገኙ ሀገራት እጅግ በጣም ብዙ ሀብቶች እንደሚመዘበሩና በዚህ ችግር ውስጥም እየዳከሩ እንደሚገኙ በርካታ ጥናቶች እንደሚያሳዩ ጠቅሰው አለማችን ለመሰረታዊ ፍላጎት የሚሆን በቂ ሃብት ቢኖራትም ጥቂቶች በስግብግብነታቸው የተነሳ የብዙሃኖችን ሃብት በመመዝበር ያለቅጥ በማከማቸታቸው ምክንያት ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንዳይኖር፣ የሰዎች የእርስ በርስ ግንኙነት እንዲደፈርስና በየቦታው ግጭት እየነገሰ እንዲመጣ ሆኗዋል ብለዋል፡፡አክለውም እንደሀገር ከዚህ ቀደም በመንግስት መዋቅር የነበረው ሙስና በፊደራል ደረጃ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም በአብዛኞች የክልል መዋቅሮች ግን ጎልቶ መቀጠሉን ተናግረው እኛም እንደከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሌሎች ላይ ጣት ከመቀሰር ቀድመን እራሳችንን በመፈተሽ በሙስና እና ብልሹ አሰራር ባለመሳተፍ እና ጥፋቶች ሲኖሩም በመጠቆም በተግባር ልንታገል ይገባል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ገናሌ ሙስናን መታገል በተግባር እንዴት ይቻላል በሚል ሃሳብ ላይ የመወያያ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን ተሳታፊዎችም የተለያዩ ነጥቦችን አንስተው ተወያይተዋል፡፡

በመጨረሻም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ እንደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ከከፍተኛ አመራር ጀምሮ መምህራኖችና የአስተዳደር ሰራተኞች ለስራ የተመደበላቸውን ጊዜና ሰዓት እንዲሁም መገልገያ ቁሳቁሶችን በአግባቡ ከመጠቀም አንስቶ ሙስናን እና የስነ ምግባር ብልሽቶችን በመጋፈጥ እና ተማሪዎችም በስነ ምግባር የታነፁ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበውና የሰራ መመሪያ ሰጥተው ፕሮግራሙ መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et