በዶሮ እርባታ ላይ የተሠሩ ሥራዎችን ተጎበኙ

የማህበረሰብ አገልግሎት በቦርቻ ወረዳ በዶሮ እርባታ ላይ የተሠሩ ሥራዎችን አስጎበኘ።

ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማኀበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቴር አቶ ማርቆስ ፍስሃ በዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጂ መንደሮች የተሰሩ የዶሮ እርባታ ሥራዎችን በቦርቻ አስጎብኝተዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ሲያስጎበኙ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተመረጡ አከባቢዎች የህብረተቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የሚያግዙ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፤ በዶሮ እርባታና በሌሎች ከአከባቢው አየር ሁኔታ ጋር ተስማም በሆኑ ዘርፎች ህብረተሰቡን በማሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡ ለአብነት በቦርቻ ወረዳ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው የወጡ ወጣቶች በማህበር ተደራጅተው ዩኒቨርሲቲው ባቀረበላቸው ምርጥ ዝርያ የዶሮ እርባታን በማካሄድ ራሳቸውንና አካባቢውን በሚጠቅም ተግባር ተሰማርተዋል፡፡

የቦረቻ ወረዳ አስተዳደር ተወካይ አቶ አሳመራ አመኖ በበኩላቸው በወረዳው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሥራ አጥ ወጣቶች መኖራቸውን ገልፀው የተወሰኑት በዩኒቨርሲቲው ስር በተቋቋመው የቴክኖሎጅ መንደር በዶሮ እርባታ ዘርፍ ተሰማርተው በዩኒቨርሲቲው ድጋፊ የአንድ ቀን ጫጩት በመውሰድና በመንከባከብ በ48 ቀናት ውስጥም ወደ ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡  

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ በዚሁ ወቅት  ባደረጉት የማጠቃለያ ንግግር  ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ጊዜያት በደረጋቸው መጠነ ሰፍ የምርምር ሥራዎች በእንስሳት መኖ ማምረት ዘርፍ ልዩ ዕውቅና ከማግኘቱም በላይ በቀጣይ ምርቱን ለመጀመር የሚያስችል ፈቃድ ከሚመለከተው አካል ማግኘቱን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ከአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ፣ በተለይም ሥራ አጥ ወጣቶችን ወደ ሥራ በማስገባት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

ተደራጅተው በዶሮ እርባታ ዘርፊ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ የቦርቻ አካባቢ ወጣቶች በዚሁ ወቅት በሰጡት አስተያየት የተጀመረው ሥራ ራሳቸውን እንዲችሉና ከቤተሰብ ጫና እንዲላቀቁ ያስቻላቸው መሆኑን ገልፀው በመኖ አቅርቦትና ተያያዥ መስኮች ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚሹ ተናግረዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et