በግጭት ጥንቁቅነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች  በግጭት ጥንቁቅነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ሰላም ተቋምና ከLife and peace Institution ጋር በመተባበር የግጭት ጥንቁቅነት አመራር ክህሎትን በሚመለከት ለመምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች በሀዋሳ ሳዉዝ ስታር ሆቴል ለተከታታይ ሶስት ቀናት ስልጠና ሰጥቷል።

በኢትዮጵያ ሰላም ተቋም ከፍተኛ የሰላም ፕሮጀክት ባለሙያ አቶ ጌትነት አማረ ስልጠናዉ የግጭት ጥንቁቅነት አመራር ላይ እና ስለ ሰላም ምንነትና አስፈላጊነት፣ ግጭትን ስለመረዳትና በግጭት አፈታት ላይ፣ የአመራር ክህሎት ምንነትና አይነቶችን ላይ በሰፊዉ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል። አክለዉም ሰልጣኞችም ከስልጠናዉ ያገኙትን ግብአት በመጠቀም አሰራራቸዉን በመከለስ ግጭትን የሚያባብሱ ዉሳኔዎችን እንዳይወስኑ፣ በሰላማዊዉ የመማር ማስተማር ሂደት እና የማህበረሰብ አገልግሎት ላይም ተግባራዊ እንዲያደርጉት እንደሚረዳቸዉ ተናግረዋል።

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et