ለተመራቂ ተማሪዎች በስራ ዝግጁነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመቀጠር ምጣኔ ማጎልበቻና የሙያ ማበልፀጊያ ማዕከል ከደረጃ ዶት ኮም ጋር በመተባበር የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችን ወደ ስራ አለም እንዲቀላቀሉ ለማስቻል ስላዘጋጃቸው ተከታታይ የስልጠና መርሐግብሮች ገለጻ ለማድረግና ግንዛቤ ለመፍጠር ያሰናዳው ፕሮግራም ጥቅምት 7/2017 በዋናው ግቢ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሂዷል።

የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ኢ/ር ፍስሐ ጌታቸው በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት የዩኒቨርሲቲዎች ዋነኛ ስራ ተማሪዎችን አስተምሮ ማስመረቅ ብቻ አለመሆኑን በመገንዘብ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከደረጃ ዶት ኮም ጋር በመተባበር ተመራቂ ተማሪዎችን ወደ ስራ እንዲቀላቀሉ በማዘጋጀት ብሎም የራሳቸውን ስራ መፍጠር እንዲችሉ የግቢ ቆይታቸውን ሳያጠናቅቁ በፊት በርካታ ስልጠናዎችን ያዘጋጀ መሆኑን አስረድተዋል።

የመ/ም/ማ/ሙ/ማ/ማዕከል ካውንስለር መ/ር ክብረት ፍቃዱ በበኩላቸው ተመራቂ ተማሪዎች ወደ ስራ ሲገቡ የሚረዷቸውን የስራና የህይወት ክህሎት ቁልፎች በሚዘጋጁ ስልጠናዎች ቀድመው መካፈላቸው ከስራ ገበያው ጋር ራሳቸውን አስማምተው እንዲጠብቁ እንደሚረዳ ገልጸዋል። ስልጠናው አመቱን ሙሉ በሚሰጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች እንደሚጀመርና በአመቱ መጨረሻም ቀጣሪ ድርጅቶችን ወደ ግቢው በመጋበዝ ተመራቂዎችን ከአሰሪዎች ጋር የማገናኘት ስራ እንደሚሰራ የጠቆሙት ኃላፊው ከምረቃ በኋላም የስልጠናውን ተጽዕኖና የመቀጠር ምጣኔ ለውጡን ለመገምገም የዳሰሳ ጥናት እንደሚደረግ አብራርተዋል።

በደረጃ ዶት ኮም የእጩዎች ጉድኝትና ትብብር ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ልዋም ፍሰሃዬ ተቋማቸው ከ30 በላይ ከሚሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከበርካታ ቀጣሪ ድርጅቶች ጋር በመሆን በየአመቱ የሚመረቁ አዳዲስ ተማሪዎችን የስራ ቅጥር አመቺ ሁኔታ ከመፍጠር አንስቶ ራሳቸውን ለስራው አለም በስነልቦና ደረጃ ዝግጁ እንዲያደርጉ የሚያግዙ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት ውጤታማ ስራ እየሰራ እንዳለ ተናግረዋል።

በዕለቱ መርሐግብር ላይ ከተለያዩ ተቋማት የተጋበዙ ኃላፊዎች ለተመራቂ ተማሪዎች የስራውን አለም ሁኔታና ከተማሪው የሚጠበቀውን ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያና የተሞክሮ ማካፈል መርሃግብር ተካሂዷል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et