አይ.ሲ.ቲ ዳይሬክቶሬት በተማሪዎች አገልግሎት ዲጂታላይዜሽን ላይ ስልጠና ሰጠ::

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአይ.ሲ.ቲ ዳይሬክቶሬት የግቢ መግቢያ በር እና የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ላይ ተግባራዊ እንዲሆኑ በራሱ ባለሙያዎች በበለጸጉ የሶፍትዌር ሲስተሞች አጠቃቀም ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ተግባር ተኮር ስልጠና ለተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሰጥቷል።

የፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ አዳቶ ስልጠናውን ሲያስጀምሩ እንዳሉት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ አገልግሎቶቹን ዲጂታላይዝ ከማድረግና ከማዘመን አኳያ በርካታ እንቅስቃሴዎች እያደረገ እንደሆነና የተማሪዎች አገልግሎት አሰጣጡን ለመቆጣጠርና ለማቀላጠፍ የሚረዱ ሲስተሞችን ወደ ስራ እያስገባ ይገኛል ብለዋል። የሶፍትዌር ሲስተሞቹ ከጊዜ ቆጣቢነትና ከደህንነት መረጋገጥ ጋር የሚያስገኙትን ጥቅሞች ለመጠቀም ብሎም የሰው ኃይሉን በአግባቡ ለማስተዳደር እንዲቻል የዘርፉን ሰራተኞች በነባርና አዳዲስ ሲስተሞቹ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ አስፈላጊ መሆኑን ኃላፊው አክለዋል።

የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር እንዳልካቸው መንገሻ በበኩላቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አይሲቲ የዩኒቨርሲቲውን አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ እያደረገ ይገኛል ካሉ በኃላ የአይሲቲ ሶፍትዌር ልማት ክፍሉ ለዩኒቨርሲቲው ብቻ ሳይሆን ለከተማ አስተዳደሮች፣ ክልሎች እንዲሁም ለሀገር አቀፍ ተቋማት ሁሉ የለተያዩ ሶፍትዌሮችን አበልፅጓል ብለዋል። አቶ እንዳልካቸው አክለውም ክፍሉ ከዓመታት በፊት ያበለፀገውና ብዙ ችግሮችን ከፈታልን ከ SIS (Student information system) ሲስተም ጀምሮ በርካታ ሲሰተሞች በዩኒቨርሲቲያችን ተሰርተው ወደ ተግባር እንደገቡ አስታውሰው የዛሬውም ስልጠና ዋናው አላማ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ወደ ተግባር በገባው የተማሪዎች ካፍቴሪያ ማኔጅምንት ሲስተም ላይ በአዲስ መልክ ስለተሻሻለው አገልግሎት ለተጠቃሚዎች ማስተዋወቅ እና በሁሉም ግቢ ሲስተሙ በእኩል መንገድ ተፈፃሚነት እንዲኖረው ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል። ይህም ሲስተም በካፍቴሪያ አገልግሎት ላይ ያለውን አገልግሎት ቀልጣፋ፣ ጊዜ ቆጣቢ፣ ብክነት ቀናሽ፣ አላስፈላጊ ወጪዎችን የሚያድን ስለሆነ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et