የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የስትራቴጂክ ጉዳይ ስራ አስፈጻሚዎች የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ፡፡

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የስትራቴጂክ ጉዳይ ስራ አስፈጻሚዎች የምክክር መድረክ ተጠናቋል::

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተ/ፕሬዚደንት ዶ/ር ችሮታው አየለ በማጠቃለያው መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የስትራቴጂክ ጉዳይ ስራ አስፈጻሚዎች  የዩኒቨርስቲውን አመራር መስመር የሚያስይዙ ቁልፍ የስራ ክፍል መሪዎች በመሆናቸው ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኮ የተሰጧቸው ተግባራት ላይ በማትኮር ውጤታማ እንዲሆኑና ወደ ራስ ገዝነት በሚደረገው ጉዞ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለይቶ በማረም ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

ፕሬዚደንቱ በአሁኑ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ አመራር ስትራቴጂያዊ ስራ ከመስራት ይልቅ ለተማሪዎች የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት ብዙ ሰዓት እንደሚያጠፋ ገልጸው አመራሩ ትኩረቱን በአንድ አቅጣጫ ላይ አድርጎ ለመጓዝ እየተተገበረ ያለው የትኩረት መስክ ልየታ ለውጥ እንደሚያመጣ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስትራቴጂክ ጉዳይ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ ቡርቃ በበኩላቸው  ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር ከተሰሩ ዋነኛ ስራዎች መካከል አንዱ የሆነው የ2017 ዓ.ም የትምህርት ሚኒስቴር የለውጥ አጀንዳዎች መነሻ በማድረግ የተዘጋጀው መሪ ዕቅድ ምን እንደሚመስል፣ ትግበራው በምን ደረጃ ላይ እንዳለና የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ከተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ቀርቦ መገምገሙን ገልጸዋል።

በመጨረሻም ሁሉም የመድረኩ ተሳታፊዎች የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅን የጎበኙ ሲሆን የተለያዩ የስራ ክፍሎችን አስመልክቶ በኮሌጁ ኃላፊዎች ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et