የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር ተወያዩ::

በክቡር ሚኒስትሩ የተመራው የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ቡድን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል አባላትና መምህራን ጋር ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም በዋናው ግቢ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ውይይት አካሂዷል::

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተ/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ እንግዶቹንና የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ ክቡር ሚኒስትሩ የውይይቱን ማስጀምሪያ ንግግር አድርገዋል::

ክቡር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዳሉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እውነትና ዕውቅት ብቻ የሚፈልቅባቸው እንዲሆኑና ምሁራን በጎታችና ኋላ ቀር አስተሳሰብ ሳይሸነፉ ነፃና ገለልተኛ በሆነ መልኩ የምርምር ስራዎቻቸውን እንድያካሄዱ በግልጽነት መስራት  ይጠበቅባቸዋል ። የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጨምሮ አሁናዊ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያላቸው: በእውቀት የተደገፈ ክርክርና ውሳኔ በሚፈልጉ ወሳኝ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምርምር መስራት: የውይይትና ክርክር መድረኮችን ማዘጋጀት: ፖሊሲ አውጭዎች ከግንዛቤ እንዲያስገቧቸው ምሁራዊ አቅጣጫ መስጠት: እንዲሁም ለአከባቢው ማህበረሰብ በየጊዜው የተሻለ ሃሳብ በማቅረብና በማወያየት ሕዝቡን ማንቃት የከ/ት/ተቋማት ዋነኛ አጀንዳ እንዲሆን ሁሉም ተግቶ እንዲሠራ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

የኑሮ ውድነትና የደመወዝ ጭማሪውን አለመጣጣም ጨምሮ የትምህርት ዘርፉን እየተፈታተኑ ነው በተባሉ የተለያዩ አስተዳደራዊና የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቷል::

ፕ/ር ብርሃኑ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ "ዛሬ እዚህ የተገኘሁት ምንም እንኳን በኢኮኖሚ ጫና ብሎም በተለያዩ አካባቢያዊና ወቅታዊ ችግሮች ብትፈተኑም በተቻለ መጠን በችሎታችሁና በእውቀታችሁ የምትተማመኑ ምሁራን: የእውቀት ጥማት ያላችሁ እና ቀጣይ ትውልድን በመቅረፅ ሀገርን የማሻገር አደራ የተጣለባችሁ እንደሆናችሁ ለማሳሰብና ልማፀናችሁ ነው!" ብለዋል::

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ክቡር ዶ/ር ሰለሞን አበርሃ በሰጡት ምላሽ እንደሀገር የትምህርት ሴክተሩ ሪፎርም በሰፊው እየተሰራበት መሆኑን ጠቁመው አሁን ያለው የሲቪል ሰርቪስ አሰራር ሁሉም ሴክተር ተመሳሳይ ቅርፅ እንዲኖራቸው ተደርጎ ስለሆነ ይሄንን የሚቀይርና ትምህርት-ተኮር የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበት በማሳወቅ መዋቅሩ ምን መምሰል እንዳለበት ለማመላከት በሰፊው እየተሰራበት እንደሆነ ገልፀዋል::

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው የተጀመረው የትምህርት ሪፎርም ቀጣይነት እንዲኖረው ሥርዓቱ የሚቀየረው ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ባሳተፈ መልኩ ባለው አጠቃላይ ኢኮ ሲስተም ይወሰናል እንጂ ትምህርት ሚኒስቴር ብቻውን የሚሰራው እንዳልሆነ ገልፀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለይ ወደ ራስገዝነት በሚያደርጉት ሽግግር ከምርምር አንፃር: ከባለድርሻ ሴክተሮች ጋር ባላቸው ትስስርና ተመራጭነት: ከደንበኛ እርካታ አንፃር ምን ቅርፅ ሊኖራቸው ይገባል በሚለዉ ላይ በዝርዝር እየተሰራ በመሆኑ ሪፎርሙ ይቀጥላል ብለዋል::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et