ለመካከለኛ ደረጃ አመራሮች ሁለተኛ ዙር ስልጠና ተሰጠ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምር/ቴ/ሽ/ም/ፕ/ጽ/ቤት የኢንተርፕሩነርሺፕና ቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ዳይሬክቶሬት ከኢንተርፕሩነርሽፕ ልማት ኢንሲቲትዩት ጋር በመተባበር ”ፐብሊክ ኢንተርፕሩነርሽፕና ኢኖቬሽን ኢኮሲስተም ግንባታ“ በሚል ርዕስ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተወጣጡ መካከለኛ ደረጃ አመራሮች ያዘጋጀው ሁለተኛ ዙር ስልጠና ከጥቅምት 1/2017 ዓም ጀምሮ እየተሰጠ ነው፡፡

የኢ/ቴክ/ማ/ዳ/ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አሰፋ ተቋማት ስልጠናውን ሲያስጀምሩ እንዳሉት የተቋማት ስኬታማነት በአመራሮቻቸው ብቃትና ማንነት ላይ የሚመሰረት እንደመሆኑ አንጋፋና ውጤታማ የሆነውን ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲን የሚመሩ ሁሉም አመራሮች የሚሰሩበትን የስራ ከባቢ በአግባቡ የተረዱና ለሚፈጠሩ ችግሮች አግባብነት ያለው መፍትሔ የሚሰጡ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ብቃትና ክህሎት ሊጨብጡ ይገባል። ይህንን ስልጠና የሚወስዱት በመጀመርያው ዙር ያልተሳተፉ አመራሮች መሆናቸውና አሰልጣኞቹ ከኢንተርፕሬነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር የሚሰሩ የራሱ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች መሆናቸውን የጠቀሱት ዶ/ር ቴዎድሮስ በርካታ መሰል ሀገር አቀፍ ስልጠናዎችን የሰጡና ልምድ ያካበቱ በመሆኑ ሰልጣኞች እድሉን እንዳያባክኑ አሳስበዋል።

ዋና አሰልጣኝ የሆኑት ኢ/ር አባተ ኃይሉ በበኩላቸው እንደ ሀገር የሚታይብንን የተቋም አመራር ክፍተት በተለመደው አሰራር በመሄድ የተለየ ለውጥ ማምጣት ስለማይቻል በሀገር አቀፍ ደረጃ በስራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካኝነት ላለፉት ሶስት አመታት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጀምሮ በተለያዩ የመንግስት መዋቅሮች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ አመራሩን የማብቃት ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አሰልጣኙ አክለውም ስልጠናው አመራሩን በስራ ፈጠራ አመለካከት የተቃኘ የስራ ባህል እንዲከተል በማድረግ በግል ራሱን በአመለካከት ለውጦ በተጨማሪም አስቻይ ከባቢን በመፍጠር ውጤት እንዲያስመዘግብ ከማስቻሉ ባሻገር አጠቃላይ ተቋማዊ ቁመናን ለማሳደግ እንደሚረዳ ተናግረዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et