በዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚደንት ዶ/ር ችሮታው አየለ የተመራው የከፍተኛ አመራር ቡድን መስከረም 29/2017 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት የተለያዩ ምልከታዎችንና ውይይት አድርጓል።

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ኢ/ር ፋሲካ ቤተ ለአመራሮቹ ስለ ኢንስቲትዩቱ አመሰራረትና አሁናዊ ቁመና ብሎም ስለትኩረት አቅጣጫዎቹ አጠቃላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን አመራሩ ከኢንስቲትዩቱ የስራ ኃላፊዎችና መምህራን ጋር በመሆን ጠቅላላውን ምድረግቢና ህንፃዎች፣ ቤተሙከራዎች፣ የሜካኒካል ምህንድስና ማምረቻና የተግባር ትምህርት ማዕከል፣ ቤተ መፃሕፍት፣ የቴክኖሎጂ ቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል፣ የተማሪዎች ማደሪያና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ ወደ ግብረመልስና ውይይት ተመልሰዋል::

ኢንስቲትዩቱ በሙሉ አቅሙ እንዲሰራና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ የኮምፒውተርና የኢንተርኔት ዝርጋታን በተለያዩ ህንጻዎች ላይ ማስፋፋት፣ የመምህራን አቅም ለመገንባትና ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት እንዲሁም ሶስተኛ ዲግሪ ያላቸው መምህራን ቁጥር በማሳደግ የምርምር ተሳትፎን መጨመር እንዲቻል ከፍተኛ አመራሮቹ ድጋፍ እንዲያደርጉ በኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ጥያቄና አስተያየት ቀርቧል።

ተ/ፕሬዝዳንቱና ም/ፕሬዝዳንቶች በውይይቱ ማጠቃለያ ወቅት ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል የቴክኖሎጂና ምህንድስና ዘርፉ የመንግስትም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲም ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ እንደመሆኑ ኢንስቲትዩቱ በተቀመጡለት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በማተኮር ሀገራዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንዲችል ሁሉም በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ህጋዊ አሰራርን ተከትለው በልዩ ትኩረት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ዶ/ር ችሮታው በማጠቃለያው በሰጡት የስራ መመሪያ ዩኒቨርሲቲዎች በአሁኑ ሰዓት ወደ ጎን ከመስፋት ይልቅ ወደ ውስጣዊ ጥራት ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው: የትምህርትም ሆነ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ለማረጋገጥ ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትም ሆነ ሌሎች ኮሌጆች የምርምርና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶቻቸውን ወደ ገቢ ማመንጫነት መቀየርና የውስጥ አቅማቸውን ማጠናከር ቅድሚያ ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበት: በተለይም ደግሞ ህንፃዎችና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ከተሰሩ በኃላ የአገልግሎት ዘመናቸውን እያሳጠረ ያለውን የፍሳሽ ማስወገጃ ሲስተም እንደ ሀገር ራሱ በሰፊው የሚታይ ችግር መሆኑን የታዘቡት እንደሆነ አንስተው የምህንድስና ባለሙያዎቹ በዚህ ችግር ላይ መፍትሄ ለማምጣት ምርምር እንዲሰሩ ጭምር አመላክተዋል:: በሌላው ምልከታቸው ደግሞ እንደባህል በሚመስል መልኩ በፅዳት ላይ አናሳ አመለካከት እንደሚስተዋል የገለፁት ተ/ፕሬዝዳንቱ ይሄ በማስተማርም: የንፅህና መጠበቂያ ግብዓቶችን በማቅረብም: ቁጥጥርና ክትትል አድርጎ በማስፈፀም ትኩረት የሚሻ ነው ብለዋል::

እዚህ ካምፓስ ያለው ከራሱ አልፎ ለከተማው ብሎም ለሀገርም የሚተርፍ እውቀትና አቅም ያለው የተማረ ኃይል እንዳለ እረዳለሁ ያሉት ዶ/ር ችሮታው ሁሉም እንደአዲስ ወደ ውስጡ እንዲያይና በራሱ አቅም መፍታት የሚችለውን ችግር ግዜ ሳይሰጥ መፍታት እንዳለበት አደራ ብለዋል:: የአካዳሚክ በተለይ ደግሞ የአስተዳደር ሰራተኞች ሕግና ኃላፊነታቸውን በሚጠበቀው ልክ ያለመረዳት ሁኔታዎች መኖራቸውን የገለፁት ተ/ፕሬዝዳንቱ ይሄንን ክፍተት ለመሙላት ሥራ መስራት በኃላም ግዴታውን በአግባቡ ያልተወጣውን አካል ተጠያቂ ወደ ማድረግ እንሄዳለን ሲሉ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et