የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማና ዉይይት መድረክ ተካሄደ

የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የ2015 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማና ዉይይት መድረክ አካሄደ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የ2015 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ የኮሌጁ ካዉንስል አባላት እና ሌሎች የሚመለከታቸዉ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ዉይይት ተካሂዷል፡፡ የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ዘለቀ አርፍጮ በመክፈቻ ንግግራቸዉ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ስብ ኮሌጅ በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የተሰጠዉን ተልዕኮ ለማሳካት ባለፉት 6 ወራት ዘርፈ-ብዙ ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱን ገልጸዉ ለዚህም የኮሌጁን ማህበረሰብና አመራር አመስግነዋል፡፡ አክለዉም strategic የትኩረት መስኮቻችንን ለማሳካት ታቅደዉ የተሰሩ ስራዎች እና የተገኙ ዉጤቶችን በዉይይቱ በዝርዝር በመገምገም በጉድለቶቻችን ላይ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የኮሌጁ የዕቅድና መረጃ አስተዳደር ኃላፊ ዶ/ር ማሙዬ በልሁ እንደገለጹት ሪፖርቱ የተዘጋጀዉ ዘጠኙን ግቦች መነሻ በማድረግ ሲሆን ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ላለፉት 6 ወራት በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እና በስትራቴጅካዊ አጋርነት በርካታ ሰራዎች ተሰርተዋል፡፡ በመማር ማስተማር ዘርፍ የዓመቱን ትምህርት በታቀደዉ አግባብ ማስኬድ ከመቻሉም በላይ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች በአገር-አቀፍ የመዉጫ ፈተና ዉጤታማ መሆን እንዲችሉ ለማድረግ ዘርፈ-ብዙ ስራዎች በልዩ ትኩረት እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍም በበጀት ዓመቱ የተሻለ እንቅስቃሴ ከመኖሩም ባሻገር የኮሌጁ መምህራን ባለፉት 6 ወራት በታዋቂ ጆርናሎች የምርምር ስራዎችን ማሳተማቸዉንና በርካታ መምህራን ፕሮፖዛል ቀርጸዉ የምርምር ስራዎችን እያከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በአጋርነት የሚሰሩ የምርምር ስራዎችም መሻሻል አሳይተዋል ያሉት የሪፖርቱ አቅራቢ በማህበረሰብ አገልግሎት ረገድም የተለያዩ ስልጠናዎች የተሰጡ መሆኑን አማላክተዋል፡፡ አለምአቀፍ አጋርነትን በተመለከተ በቻይንኛ ትምህርት ክፍል በኩል ከኮንፊሸስ ተቋም ዳይረክቶሬት ጋር አብሮ ለመስራት ከስምምነት መደረሱን እና  ከBritish Council ጋር በመተባበር IELTS ማዕከል ለማቋቋም እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ከተሳታፊዎቹ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ዘለቀ አርፍጮ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በበጀት ዓመቱ 6 ወራት ያሳካናቸዉ ተግባራትን በማጠናከር በታዩ ክፍተቶቻችን ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተን በመስራት  በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በርትቶ መስራት የሚጠበቅ መሆኑን በማሳሰብ የግምገማና ዉይይት መድረኩን ማጠቃለላቸው ታውቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et