ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ::
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰኔ 25/2016 ዓ.ም ተፈራረሟል::
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ኢንስቲትዩቱ በውሃ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከፍተኛ አቅም ያላቸው ባለሙያዎች ካሉት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት በመምጣቱ አመስግነው እንደሀገር እጅግ ጠቃሚ በሆኑ የውሃ ቴክኖሎጂዎች ላይ እንደ አጋር ተቋማት ተቀራርቦ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል::
የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታመነ ኃይሉ በፊርማው ወቅት እንደገለፁት ለሴክተሩ እጅግ ጠቃሚ የሆነ ግብዓት እና የፖሊሲ አቅጣጫ ጠቋሚ የሆኑ የምርምርና ቴክኖሎጂ ስርፀት ስራዎችን በሰፊው አብሮ ለመስራት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሃገራችን ካሉ እምቅ አቅም ያላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ስምምነቱ ከዚህ ቀደም የነበረውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ይረዳናል ብለዋል::