በደቡብ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ልማት ላይ ያተኮረ ኮንፍረንስ ተካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ጋር በመተባበር አመታዊ ኮንፍረንስ በሀዋሳ አካሄደ፡፡

በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ ት/ት ክፍል ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን-ደቡብ ቻፕተር  ጋር በመተባበር በደቡብ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ልማት ላይ ያተኮረ 10ኛውን አመታዊ ኮንፍረንስ በመጋቢት 17/2014ዓ.ም በሀዋሳ አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ስሜነህ በሲ አሶሴሽኑ ከተመሰረተበት 1983ዓ/ም ጀምሮ  ከ5100 በላይ አባላት እና ሰባት ክልላዊ ቻፕሮች እንዳሉት ገልፀው  ለሀገር ግንባታ አስፈላጊ ፋይዳ ያላቸውን አጀንዳዎች በመቅረፅ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ትስስር በመፍጠር፣ ተጨባጭና ችግር ፈቺ ምርምሮችን በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና አካባቢጉዳዮች ላይ በማድረግና ጉባኤዎችን በማዘጋጀት ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር ውይይትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማመላከት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በመክፈቻ ንግግራቸው በዚህ ኮንፍረንስ በደቡብ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ልማት ያሉ አማራጮችን፣ ውስብስብ ችግሮችን እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ከሚቀርቡት የጥናት ውጤቶች በጥልቀት ለመረዳት፣ ለመፈተሸና የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም ለመምከር የሚያስችለን ሲሆን ዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽኑ የዚህ መሰሉን የውይይት መድረክ እንዲያዘጋጅ በምርምር ስራዎች፣ ስልጠና በመስጠት፣ ምሁራንን በማሳተፍ፣ የጥናት ውጤቶችንም በማሳተም  እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስራት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

በፕሮግራሙም ላይ በጥናት አቅራቢዎች ስለ ኢትዮጵያ ዋጋ ግሽበት ሰፋ ያለ ጥናት አቅርበው በሀገሪቱ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ ብዙ ገንዘብ ወደገበያ መግባቱ እና የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት ለግሽበቱ እና የገብያ ዋጋ ንረት ምክንያቶች ውስጥ ተጠቃሽ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በኮንፍረንሱ ላይ በደቡብ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዙሪያ ዘርፈ ብዙ ጥናታዊ ፅሁፎች በባለሙያዎች ቀርቦ እና ከተሳታፊዎችም ጋር ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

 

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et