የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አደረገ

የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከኮሌጁ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረገ፡፡

ሀዋሳ፣ ጥር 07 ፣ 2014ዓ.ም የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በ2014ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን አፈፃፀም ሪፖርት ለኮሌጁ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች አቅረርቦ ውይይት አድርጓል፡፡

ኮሌጁ በሰው ሀይል ልማት፤ በመማር ማስተማር ግብዓት አቅርቦት፤ብቁ እና ተወዳዳሪ ተመራቂ  ከማፍታት አንፃር እንዲሁም ዓለም አቀፍ አጋርነትን ከማጠናከር አኳያ ኮሌጁ ጠንካራ አፈፃፀም ያሳየባቸው መለኪያዎች መሆናቸውን የኮሌጁ የመረጃ አስተዳደር ኃላፊ ዶ/ር ማሙዬ በልሁ አስተድረተዋል፡፡ አክለውም ሀገራዊ አከባቢያዊ ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ ችግር ፈቺ ምርምሮችን እና የፈጠራ ስራዎችን በማጎልበት ረገድ ብሎም የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች  ኮሌጁ ትኩረት ሰጥቶ በ6ወር አፈፃፀሙ መስራት የቻለባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ዶ/ር ማሙዬ አብራርዋል፡፡

በቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርት መነሻነትም ከመምህራን እንዲሁም አስተዳደር ሰራተኞች ጥያቄ እና አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡ በተለይም ለመማር ማስተማር ስራ አጋዥ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ፤ ከክፍያ ስርዓቱ ጋር በተያያዘ እየተፈጠሩ ያሉ የክፍያ መንጓተቶች እንዲሁም በፈተና ጥራት እና ቁጥጥር የተነሱ ጥያቄዎች ዋነኞቹ ናቸው፡፡

ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በምርምር ዩኒቨርስቲነት ከተመረጡ የሀገራችን ከፍተኛ የት/ት ተቋማት መካከል አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡በዚህም በ6 ወራት አፈፃፀም በተለያዩ የት/ት መስኮች በ2ተኛ እና 3ተኛ ድግሪ መማር ማስተማር ስራ ለማስጀመር የሚያስችሉ ተግባራት መከናወን መቻሉን የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዳኜ ገልፀዋል፡፡ በመጀመሪያ ድግሪም በቲያትር እና ፊልም ጥበባት የትምህርት መስክ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተው ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በዝግጅት ላይ እንዳለ አክለው አብራርተዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ  ከእቃዎዎች ዋጋ መናር ጋር የተያያዘ በመሆኑ  ያሉ ችግሮች የሚስተካከልበት አግባብ እንዲፈጠር እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም ከክፍያ ስርዓት ምንጓተት ጋር እየታየ ያለው ችግር በመሰረታዊነት አዲስ ከተዘረጋው የክፍያ አሰራር ግር ከመላመድ ጋር የሚያያዝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡የተሠጡ ገንቢ አስተያየቶችን በመውሰድ  ለቀጣይ ስድስት ወር በትኩረት እንደሚሰራባቸው ዶ/ር ዳኜ አስገንዝበዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et