የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የ2014 የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ

የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የ2014 የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።

በጽ/ቤቱ ሥር የሚገኙ ሥራ ክፍሎች የግማሽ ዓመት ሥራ አፈጻጸማቸውን የገመገሙበትን መድረክ የመሩት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ፍስሐ ጌታቸው ከመጀመሪያ እስከ 3ኛ ዲግሪ በመሰጠት ላይ የሚገኙ ነባር የትምህርት ፕሮግራሞችን መከለስ እና መምህራን የትምህርት ዕድል እንዲያገኙና ራሳቸውን በዕውቀት እንዲጎለብቱ ማድረግ ትኩረት የተደረገባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በተለይም በጦርነቱ አካባቢ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎችን በመቀበል ተረጋግተው እንዲማሩ ድጋፍና ክትትል የማድረግ ሥራ ከመከናወኑም በላይ በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ከጥሬ ገንዘብ በተጨማሪ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ከዩኒቨርሲቲው ማኀበረሰብ ሰብሰቦ ግንባር ድረስ በማቅረብ የሀገር ደጀንነት ለመግለጽ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በትምህርት ዘርፍ የምርምር ሥራዎች ኩረጃ /plagiarism/ ለማስቀረት ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑ በዚሁ ጊዜ የተገለጸ ሲሆን ከፍተኛ በሆነ ወጪ አዳዲስ የክለሳ ዋቢ መጻሕፍቶች በክፍተኛ ወጪና በእርዳታ መልክ ወደ ቤተ መጻሕፍት የገቡ ብሆንም ተማሪዎች ከሞባይል በማንበብና በአጠቃላይ በሶፍት ኮፒ ላይ ጥገኛ መሆናቸው ለትምህርት ጥራት ተጨማሪ ተግዳሮት እየሆነ መምጣቱ በመድረኩ  ተመልክቷል፡፡

በቀጣዮቹ 6 ወራትም የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ከመሆናቸውም በላይ ሁሉም ኮሌጆችና የትምህርት ክፊሎች የመምህራን ልማት ስራ ዕቅዶቻቸውን እንዲያጎለብቱ በትኩረት የሚሠራ መሆኑ ተገልጾአል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et