የ"Milk Run" የስራ ፈጠራ ኤክስፖ ተካሄደ

አመታዊው የ"Milk Run" የዩኒቨርሲቲ የስራ ፈጠራ ኤክስፖ ተካሄደ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የክህሎት ማበልፀግያ ማዕከል ከደረጃ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በዋናው ግቢ ሰኔ 25/2016ዓ.ም ያዘጋጀው የሥራ ኤክስፖ የዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች፣ የኢትዮ ጆብስ ሰራተኞች፣ የቀጣሪ ድርጅቶች ተወካዮች እና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ተመራቂ ተማሪዎች ተሳትፈውበታል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ኢ/ር ፍስሀ ጌታቸው በመክፈቻ ንግግራቸው ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ የሚያስመርቃቸው ወደ 5 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎቹን ከስራ አለም ጋር ለማገናኘት የሚያስችሉ መሰል ከቀጣሪ ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረጉ የትብብር ስራዎች ሚናቸው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። ኤክስፖው ቀጣሪና ተቀጣሪውን በቀላሉ ፊት ለፊት የሚያገናኝ በመሆኑ በስራ ፍለጋ የሚባክነውን ጊዜ እንደሚያሳጥር የገለፁት ም/ፕሬዚደንቱ ይህም በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የስራ አጥነት መበራከት እንደሚቀንስ ተናግረዋል።

የኢትዮ ጆብስና ደረጃ ዶት ኮም (Ethio jobs & Dereja.com) ስራ አስኪያጅ የሆኑት  አቶ ዩሱፍ ረጃ ድርጅቱ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በትብብር በሚሰራቸው ስራዎች በየአመቱ በርካታ አዳዲስ የስራ እድሎችን ለተመራቂዎች በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻሉን ገልጸዋል። ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት አሰጣጥ ጥራቱና ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ባለው ቁርጠኝነት ከሚደነቁ ተቋማት አንዱ መሆኑን ያወሱት አቶ ዩሱፍ በለቱ ከ3 ሺህ በላይ ክፍት የስራ እድሎችን የያዙ ከ70 በላይ ቀጣሪ ድርጅቶች በኤክስፖው ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ክብረት ፍቃዱ በበኩላቸው ላለፉት ሁለት አመታት ከደረጃ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች ከስራ አለም ጋር ለማገናኘት በተሰራው ስራ የተሻለ ውጤት መገኘቱን ጠቁመው በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ተማሪዎች ቀደም ብለው በማዕከሉ አማካኝነት የተለያዩ የክህሎት ስልጠናዎችን በማግኘታቸው በቀጣሪ ድርጅቶች ዘንድ ተመራጭ እንዲሆኑ እንደሚያስችላቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et