አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶች በሀዩ ኮ/ስ/ሪፈራል ሆስፒታል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል የጥርስ ህክምና ትምህርት ክፍል አዳዲስና በህብረተሰቡ ዘንድ እጅግ ተፈላጊ የሆኑ የህክምና አገልግሎቶችን ከመስከረም 4/2016 ዓም ጀምሮ መስጠት መጀመሩን የሆስፒታሉ ቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሩ ክፍሌ ገልጹ።

ዶ/ር ክብሩ አክለውም እነዚህ የህክምና አገልገሎቶች በኢትዮጵያ በመንግሥት ሆስፒታል ደረጃ የሚሰጡት ለመጀመሪያ ግዜ መሆኑን ጠቁመው ይህም ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎቱን እንዲያገኝ ከማስቻል በተጨማሪ የሆስፒታሉን አገልግሎትና ተፈላጊነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ተናግረዋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጥርስ ህክምና ትምህርት ክፍል አባል የሆኑት ዶ/ር ግርማ ሞገስ በበኩላቸው ጥርስ እጅግ አስፈላጊ የሰውነት ክፍል በመሆኑ ከጥርስ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ህመሞች ፋታ የማይሰጡና በጊዜ መታከም የሚገባቸው መሆኑን ገልጸው ሆስፒታሉ ቀደም ሲል ይሰጥ ከነበረው የጥርስ ነቀላና የፊትና መንጋጭላ ቀዶ ህክምና (Maxillofacial surgery) በተጨማሪ አዳዲስ የሆኑትን የጥርስ እጥበት፣ ሙሌት፣ ሰው ሰራሽ ጥርስ ተከላ፣ የጥርስ ስር ህክምና እና የተዛነፉ ጥርሶችን በብሬስ የማሰር አገልግሎቶች መስጠት መጀመሩን ተናግረዋል።
ዶ/ር ግርማ አክለውም ማንኛውም ታካሚ በስፔሻሊስት ሀኪሞች የሚሰጡትን አገልግሎቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት እንደሚችልና በተለይም ለጥርስ ህመም ተጋላጭ የሆኑት የስኳርና የደም ግፊት ህመምተኞች የህክምናው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et