የአዲስ ዓመት መልዕክት ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በራሶ
ውድ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላትና አጋሮች በሙሉ:-
በቅድሚያ እንኳን ለ2016 ዓ.ም አዲስ ዘመን መለወጫ በሰላም በጤና አደረሳችሁ/አደረሰን!
እንደምታውቁት ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሐዋሳ መለስተኛ ግብርና ኮሌጅ ተብሎ ከተመሰረተበት ከዛሬ 48 ዓመት አንስቶ በነበረው የለውጥ ጉዞ ከአገልግሎት ማስፋፋት ባሻገር በርካታ የስኬት ታሪኮችን እያስመዘገበ ዛሬ ያለበት የሀገራችን አንጋፋና ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን በቅቷል::
ዩኒቨርሲቲያችን የትምህርት: ምርምርና የማህበረሰብ ጉድኝት ላይ ሀገራችን ልታመጣ ባስቀመጠችው የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም መሰረት ራስ ገዝ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ለመሆን በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል::
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ7 ካምፓሶቹ ባሉት 8 ኮሌጆችና 3 ኢንስቲትዩቶች ከ28 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ በ102 የመጀመርያ: በ141 የማስተርስ እና በ55 የዶክትሬት ዲግሪ እንዲሁም 11 የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች በመደበኛው: በተከታታይና በክረምት መርሃግብሮች በማስተማር ለሀገር እድገትና ብልፅግና የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ የሚገኝ ታላቅ ተቋም ነው:: ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ መምህራን: የአስተዳደር ሰራተኞች እና የጤና ባለሙያዎችን ያስተዳድራል::
ዩኒቨርሲቲያችን ለትምህርት: ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ጥራት ከፍተኛ ቦታ በመስጠት ከበርካታ አለምአቀፍና ሀገር በቀል ተቋማት ጋር የትብብር ስምምነት በመፈፀም በትምህርት ጥራት: በሰው ሀብት: በማቴሪያልና በመሰረተ ልማት አቅም ግንባታው ዘርፍ መጠነ ሰፊ ስራዎችን ይሰራል::
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከምርጥ 10 የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ለመሆን ራዕይ ሰንቆ የሚሰራ እንደመሆኑ በአዲሱ 2016 ዓ.ም ሁሉም የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ አካላት እንዲሁም አጋሮቻችን ከዚህ ቀደም ከነበረው በላይ በመናበብና በህብረት ሰርተን የተጣለብንን ትውልድን የመቅረጽ ታላቅ ሃገራዊ ኃላፊነት በተሻለ ብቃትና ጥራት እንድንወጣ አደራ ማለት እፈልጋለሁ::
አዲሱ 2016 ዓ.ም የጤና: የሰላም: የአንድነትና የብልፅግና እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ሰላም ይብዛላችሁ/ልን!
መልካም አዲስ አመት!
አያኖ በራሶ ሁላ (ዶ/ር)
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት
Ethiopian New Year Message from HU's President
To All Hawassa University Community and Partners:-
I wish you a very bright and happy Ethiopian New Year, 2016!
As you all know, Hawassa University has been striving to excel in ensuring quality of education, research and community engagements over the years since its very foundation as a junior agricultural college, 48 years back. Today, HU is among the most established, first generation and most preferred universities in Ethiopia nationally differentiated to be an autonomous research university.
Hawassa University has expanded its services through 8 colleges and 3 institutes distributed across its 7 campuses located within and near the beautiful Hawassa City, 275 kms south of Addis Ababa. HU offers degrees in 102 undergraduate, 141 Masters, 55 PhD and 11 Medical Speciality programs hosting 28+ thousand students enrolled in the regular, continuing and summer programs. HU has 10 thousand plus scientific, administrative and health professional staff overall.
With its vision of becoming one of the top ten African universities in 2030, the university is tirelessly working in collaboration with several international and local institutions on education, research, community service and human as well as material capacity building schemes. We are also working on reforms to transition into an autonomous research university in the coming two years following the national differentiation.
On the occasion of the Ethiopian New Year 2016, I call up on the entire HU Community and our dear partners to work in unison and harmony towards achieving our shared goals in discharging our responsibility of building generations!
I wish you all a new year full of health, peace, unity and prosperity!
Happy Ethiopian New Year!
God bless Ethiopia and its People!
Ayano Beraso Hula (PhD)
President, Hawassa University