የውይይትና ደስታ መግለጫ ፕሮግራም

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ውድድር አንደኛ መዉጣቱን አስመልክቶ የዉይይትና የደስታ መግለጫ ፕሮግራም አዘጋጅቷል።

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል በቀለ በመርሃግብሩ መክፈቻ ንግግራቸው በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ካሉት ዘጠኝ ኮሌጆችና አንድ ኢንስቲትዩት ጋር በነበረው የዕቅድ አፈፃፀም መመዘኛ ዉድድር የወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ አንደኛ በመዉጣቱ እንኳን ደስ አላችሁ አለን ብለዋል። ዲኑ የመርሃግብሩን አላማ ሲያብራሩም በዉድድር መስፈርቱ መሰረት የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖቻችን ላይ ከመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ኃላፊዎች ጋር በመወያየት ጠንካራ ጎናችንን ለማስቀጠል እንዲሁም ደካማ ጎኖቻችንን ለማረምና ለማስተካከል ሲሆን ዉጤቱን አስመልክቶም በጋራ ደስታችንን ለመግለፅ ነዉ ብለዋል።

የኮሌጁ ዕቅድና መረጃ አስተዳደር አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ በቀለ የ2015 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ምዘና ዉጤት ሪፖርት፣ የዉድድር መስፈርቶችና በአፈፃፀሙ ግምገማ ላይ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በማቅረብ መምህራንና በየደረጃዉ የሚገኙ የስራ ኃላፊዎችን ለዉይይት ጋብዘዋል።

በቀረበዉ ገለፃ መነሻም ተሳታፊዎች ዉይይት ካደረጉና አስተያየት ከሰጡ በኃላ ኮሌጁ አንደኛ መዉጣቱን አስመልክቶ የኮሌጁ ዲን እና ኃላፊዎች በውድድሩ የተገኘዉን ዋንጫና የምስክር ወረቀት ለኮሌጁ ማህበረሰብ ተወካዮች አስረክበዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et