ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የሶስት ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ሆነ።
የ2015 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የእግር ኳስ ውድድር የዓመቱ አሸናፊ ክለብ የዋንጫና የዘርፉ ከዋክብት የሽልማት ፕሮግራም በአዲስ አበባ ሀያት ሬጀንሲ ሆቴል ነሐሴ 13/2015 አካሂዷል::
ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዚሁ የሽልማት መድረክ ለፕሪምየር ሊጉ ስኬት ላበረከተው አስተዋፅኦ የሦስት ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆኗል:: ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያደረገውን አስተዋፅኦ በተመለከተ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቦርድ ሰብሳቢ መ/አለቃ ፈቃደ ማሞ ሲናገሩ መዲናዋ አዲስ አበባን ጨምሮ የፕሪምየር ሊግን እንዲያስተናግዱ የሚጠበቁት ትላልቅ ከተሞቻችን ደረጃቸውን የጠበቁ ሜዳዎች ባይኖራቸውም ሐዋሳ ላይ ዩኒቨርሲቲው ሜዳውን አዘጋጅቶ ይሄንን ችግር ስለቀረፈልን ላቅ ያለ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል::