የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ የውይይት መድረክ ላይ ከነሐሴ 8 - 9/2015 ዓ.ም በወንዶ ገነት የደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ማካሄድ ጀምሯል::

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በራሶ መድረኩን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ባለፈው የበጀት ዓመት እንደሀገር ከራሱ መደበኛ ሥራ ባሻገር ሦስት ሃገር አቀፍ ፈተናዎችን ያስተናገደ ሲሆን ስራው ብዙ ጥንቃቄ የሚፈልግና ከባድ ኃላፊነት ቢሆንም በስኬት መወጣት ችለናል ብለዋል:: በተጨማሪም ለመጀመሪያ ግዜ የተሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች አንፃር ሲታይ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአፈፃፀም ደረጃ ከሌሎቹ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እጅግ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል:: ፕሬዚደንቱ ለዚህ ሁሉ ስኬታማ ሥራ የሁሉም የስራ ክፍሎች መናበብና የጋራ ርብርብ ማድረግ ወሳኝ ስለነበር ለሁሉም የዩኒቨርሲቲው አመራርና ሰራተኞች ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል:: አክለውም የውይይትና ግምገማ መድረኩን አስፈላጊነት ሲገልፁ በዓመቱ የዕቅድ አፈፃፀም ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖች እንዲበረታቱ: ደካማ ጎኖች እንዲሻሻሉ ሃሳብና አቅጣጫ ለመስጠት እንዲሁም ቀጣዩን ዓመት የሚጠብቀንን የቤት ሥራ በግልፅ ተመካክረን ለማቀድና ለመተግበር ስለሚረዳ ነው ብለዋል::

በመድረኩ የመጀመሪያው ቀን ውሎ የአካዳሚክ ጉዳዮች: የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚደንቶች የየዘርፋቸውን አመታዊ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል:: ሪፖርቶቹን ተከትሎ በተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን ሁሉም ምክትል ፕሬዚደንቶች ጥያቄዎችን ለመመለስና በተነሱ አስተያየቶች ላይ አቋማቸውን እንዲያንፀባርቁ ዕድል ተሰጥቷቸዋል::

በማጠቃለያው ፕሬዚደንቱ በአሁኑ ሰዓት ዩኒቨርሲቲው ወደ የምርምር ዩኒቨርሲቲነት የሚያደርገው ሽግግር: አዲስ የዩኒቨርሲቲ መዋቅር ክለሳ: እና ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን የሚደረግ የዝግጅትና የሽግግር ሥራዎች በድምሩ ሦስት የማሻሻያና የሽግግር ሥራዎች በሰፊው እየተሰራባቸው መሆኑን ጠቁመው ከእነዚህ ወሳኝ የሥራ ሂደቶች ጋር አያይዘው ጠቅላላ ሪፖርትና የተነሱ ጥያቄና አስተያየቶች ላይ ዝርዝር ምላሽና ተጨማሪ የስራ መመሪያዎችን በመስጠት የዕለቱ መርሃግብር ተጠናቋል::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et