የመውጫ ፈተና ዝግጅት ግምገማ በሀዩ

የሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ሴኔት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ለመጀመሪያ ግዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የተመራቂ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና እንዲሁም የማካካሻ (ሬመድያል) ትምህርት መርሃግብር ፈተናን ለመስጠት እንደ ተቋም እያደረገ ያለውን ዝግጅት: በሂደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን የገመገመበት ሁለተኛ ዙር ስብሰባ ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም አካሂዷል::

ስብሰባውን የመሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ሁሉም ኮሌጆች እስካሁን የሰሯቸውን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሪፖርት እንዲያቀርቡ የጋበዙ ሲሆን የሚመለከታቸው ዲኖችና ዳይሬክተሮች የየክፍላቸውን ሥራ ዝርዝር ሪፖርት ለኮሚቴው አቅርበዋል::

ለግምገማው የቀረቡት ዋና ዋናዎቹ ነጥቦችም:-
• ለተፈታኝ ተማሪዎች ሁለት ዙር የመለማመጃ ሞዴል ፈተና ስለመሰጠቱ
• ለፈተና አሰጣጡ የሚያስፈልገው የኢንተርኔት መስመር ዝርጋታና ያለበት ደረጃ
• በልምምድ ፈተናው የተመዘገበው የተማሪዎች ውጤት ምን እንደሚመስል
• ከትምህርት ሚኒስቴር የወረደው ፈተናውን የሚመለከት መረጃና መመሪያ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በወቅቱ ስለመዳረሱ
• ለሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች የግል ኢሜል አካውንት ስለመከፈቱ
• አስፈላጊው የፈታኝ መምህራን ምልመላ ስለመደረጉ
• ለአካል ጉዳተኛና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተፈታኝ ተማሪዎች አስፈላጊው የድጋፍ አሰጣጥ ዝግጅት ስለመደረጉ
የሚሉት ይገኙበታል::

የሴኔት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በእነዚህና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ጠንከር ያለ ውይይት ያደረገ ሲሆን ቀሪ የዝግጅት ሥራዎች በተቻለ ፍጥነትና የኃላፊነት ስሜት ሁሉም የፈተና ግብረሃይል ተቀናጅቶ እንዲሰራባቸውና የደረሰበትን ደረጃም በቀጣይ ስብሰባ ላይ ሪፖርት እንዲያቀርብ ፕሬዚደንቱ መመሪያ ሰጥተው ስብሰባው ተጠናቋል::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et