ለተመራቂ ተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለተመራቂ ተማሪዎች ስለ ኢንተርንሽፕ ስልጠና ሰጠ።
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የም/ቴ/ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከከፍታ ዩ ኤስ አይ ዲ ኢንተርንሺፕ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የካቲት 11/2015 ዓ.ም ለተመራቂ ተማሪዎች በኢንተርንሺፕ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
 
በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የም/ቴ/ሽ/ም/ዳይሬክተር ዶ/ር ገብረክርስቶስ ኑርዬ በመክፈቻ ንግግራቸዉ እንደገለፁት የንድፈ ሃሳብ ትምህርት አስፈላጊ ቢሆንም ዉጤታማ የሚሆነዉ ያንን በተግባርና ክህሎት መደገፍ ስንችል ነው ብለዋል:: በዚህም የዩኒቨርሲቲያችን ምሩቃን ያወቁትን ለመተግበር እና አዲስ ነገር ለመፍጠር የሚችሉ እንዲሆኑ ወደስራዉ አለም ከመግባታቸዉ በፊት በንድፈ ሃሳብ ክፍል ዉስጥ የተማሩትን በኢንተርንሺፕ ስልጠናው በተግባር ተደግፎ ማየት ሲችሉ መሆኑን ተናግረዋል።
 
በኢንስቲትዩቱ የቴ/ሽ/የዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ ዶ/ር ካሳሁን ጋሹ የስልጠናዉን ዓላማ አስመልክቶ ሲናገሩ ከፍታ ዩ ኤስ አይ ዲ ኢንተርንሺፕ ፕሮግራም ባወጣዉ መስፈርት መሰረት 836 ተማሪዎችን አወዳድሮ በነጥብ ብልጫ ያገኙ 100 ተማሪዎችን በኢንተርንሺፕ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድሉን ያመቻቸ ሲሆን የዛሬዉም የግንዛቤ ማስጨበጫ የዚሁ ዕድል አንዱ አካል መሆኑን ገልፀዉ ወደፊት ተማሪዎቹ ለኢንተርንሺፕ ሲወጡም ድጋፍ እንደሚደረግላቸዉ ተናግረዋል።
 
ዶ/ር የቆየአለም ደሱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ኮሌጅ ዲን እና ከአሪዞና ዩኒቨርሲቲ የከፍታ ፕሮግራምን ለማስተባበር የተወከሉ ሲሆን የዕለቱን ስልጠና በማስመልከት ስለ ከፍታ ፕሮግራም፣ ስለወጣቶች፣ ስለ ኢንተርንሺፕ ምንነትና አስፈላጊነት እንዲሁም ከተማሪዎች በኢንተርንሺፕ ወቅት ምን ይጠበቃል የሚሉ ፅንሰ ሃሳቦች ላይ በማተኮር ስልጠናዉን ሰጥተዋል።
ከስልጠናዉም በኃላ ተማሪዎች ጥያቄዎችን በማንሳትና በመወያየት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et