ለተመራቂ ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ለተመራቂ ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሰጠ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ለተመራቂ ተማሪዎች ከየካቲት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የሕይወት ክህሎት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

 የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል በቀለ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ሲናገሩ ተመራቂ ተማሪዎቻችን ከመደበኛው ትምህርት በተጨማሪ ተመርቀው ሲወጡ ወደ ስራው ዓለም ለመቀላቀል እንዲረዳቸው በማሰብ የተዘጋጀ የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሲሆን በዚህ ስልጠናም ተመራቂዎቹ በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ብቁ በመሆን ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ፣ በዙሪያቸው ያሉትን አማራጮች እንዲጠቀሙና እራሳቸውን በተለያዩ ክህሎቶች እንዲያበቁ ከማስቻል በተጨማሪ በኑሮና በእውቀት ልምድ ያላቸው መምህራኖች የሕይወት ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሏቸው ይደረጋል ብለዋል፡፡

 የመቀጠር ምጣኔ ማጎልበቻና የሙያ ማበልፀጊያ ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ታዬ ገ/ማርያም ስልጠናውን አስመልክቶ  ስልጠናው ሰልጣኝ ተማሪዎች ከምረቃ በኃላ ቀጣሪዎች በሚፈልጉት መልኩ ስለራሳቸውና ስለተማሩት ሙያ የሚገልፅ ሲቪ አዘገጃጀት፣ ስራ አፈላለግ፣ የቃለመጠይቅ ዝግጅት፣ ማመልከቻ አፃፃፍ፣ የስራ ፈጠራ፣ የተግባቦትና ስራ አፈላለግ የመሳሰሉ ክህሎቶችን የሚዳስስ የሁለት ቀን ስልጠና ሲሆን ማዕከላችን ባደረገው ጥናት መሰረትም ቀጣሪ ድርጅቶች እነዚህን ክህሎቶች እንደሚፈልጉ በመረዳት ተማሪዎቹ ከመመረቃቸው በፊት ስልጠናውን እየሰጠናቸው እንገኛለን ብለዋል፡፡ አክለውም ከዚህ የሕይወት ክህሎት ስልጠና በተጨማሪ በዓመቱ መጨረሻ አካባቢም የስራ አውደ-ርዕይ በማዘጋጀት ቀጣሪ ድርጅቶችን እና ተመራቂዎችን በማስተዋወቅና በማገናነት የስራ ዕድል እንዲፈጠር ለማድረግ የሚሰራ ሲሆን የዚህ መሰሉ አሰራር በቀጣሪ ድርጅቶችና በተመራቂዎች መካከል የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et