ሁለተኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ ተደረገ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ኮሌጅ በ2015 ሁለተኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ አደረገ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ኮሌጅ በ2015ዓ.ም ሁለተኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ከኮሌጁ ትምህርት ክፍል፣ ትምህርት ቤትና ማዕከላት ኃላፊዎች፣ ም/ዲኖችና አስተባባሪዎች ጋር በጥር 9/2015ዓ.ም ግምገማና ውይይት አካሄደ፡፡

የትምህርት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል አሰፋ ባለፉት ስድስት ወራት የመማር ማስተማር፣ ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በታቀደው ዕቅድ መሰረት እየተከናወኑ መሆናቸውን በመግለፅ ምንም እንኳን ተደራራቢ ሃገራዊ ስብሰባና ውይይት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የነበረ ቢሆንም ኮሌጁ በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ ለመምህራን እና ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ከመስጠት አንስቶ ለተማሪዎችም የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ እንደሆነ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በኮሌጁ ትምህርት ልዕቀት አስተባባሪነት የጎልማሶች ማስተማሪያ ሞጁሎች እና የርቀት ትምህርት መማሪያ መፅሐፍቶች እየተዘጋጁ መሆናቸውን፣ አንድ ቴማቲክ ምርምርና እና አምስት ዲሲፕሊነሪ ምርምሮች በኮሌጁ ምሁራኖች እየተሰሩ መሆናቸውን እንዲሁም በምርምር ስነ-ምግባርና ጆርናል አዘገጃጀት ላይ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን ተናግረዋል፡፡ አክለውም በዚህ ሪፖርት አፈፃፀም ግምገማና ውይይት ላይ የተገኙ ኃሳቦችን በማካተት ኮሌጃችን የራሱን ቤተ-መዕሐፍት ቤት ከማደረጀት አንስቶ በቀጣዮቹ ጊዜያቶች በርካታ ስራዎች የሚጠብቁን በመሆኑ በኮሌጁ የሚገኙ መምህራኖች እና ኃላፊዎች በተሰሩት ስራዎች ሳይዘናጉ ቀጣይ ለሚቀሩን ስራዎች እራሳቸውን በማዘጋጀት ከዚህ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አደራ እላለሁኝ ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙም የኮሌጁ ትምህርት ክፍሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የም/ቴ/ሽ/ም/ዲን ፅ/ቤት፣ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን ፅ/ቤት፣ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ማዕከል፣ የመቀጠር ምጣኔ ማጎልበትና ማሻሻያና ሬጅስትራር ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀረበውም ላይ ግምገማና ውይይት እንዲሁም ቀጣይ ስራዎች ላይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ፕሮግራሙ መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et