በምርምር ስነ-ምግባርና ጆርናል አዘገጃጀት ላይ ስልጠና ተዘጋጀ

የትምህርት ኮሌጅ በምርምር ስነ-ምግባርና ጆርናል አዘገጃጀት ላይ የስልጠና መድረክ አዘጋጀ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ኮሌጅ ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም በምርምር ስነ- ምግባር እና ጆርናል አዘገጃጀት ላይ የስልጠና መድረክ  አዘጋጅቷል፡፡

የትምህርት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል አሰፋ ኮሌጁ የራሱን የምርምር ጆርናል በማዘጋጀትና ኮሚቴ በማቋቋም ከዚህ ቀደም የተለያዩ የምርምር ውጤቶችን ያሳተመ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት አዲስ የምርምር ጆርናል ኮሚቴ የተቋቋመ በመሆኑ ለአዲሶቹ የኮሚቴ አባሎችና በምርምር ጆርናሉ ላይ ለሚሰሩ አባላቶች በምርምር ስነ-ምግባርና ጆርናል አዘገጃጀት ላይ ስልጠና ለመስጠትና የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን እና በሂደት ላይ ባሉ ምርምሮች ላይም ግምገማ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

የምርምር ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ራህመቶ አበበ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ብቁና የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማብቃት ጎን ለጎን የህብረተሰቡን ችግር ፈቺ ምርምሮችን እና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ላለፉት በርካታ አመታት እየሰራ መሆኑን አውስተው የምርምር ስራዎችን በተመለከተም ከዚህ ቀደም የምርምር ስራዎች የሚታተሙበት ጆርናሎች ቁጥር ሁለት የነበረ ሲሆን አሁን ግን አስር መድረሳቸውን እና የሚታተሙ ምርምሮችም በቁጥርና በጥራታቸው እያደጉ መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ አክለውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብለው ከተለዩት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አንዱ እንደመሆኑ ምርምርን ባህላችን በማድረግ የሚሰሩ ምርምሮችም በጥራትና በቁጥር መጨመር እናዳለባቸውና ውጤቶችም በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባለው ጆርናሎች ላይ መታተም እንዳለባቸው ገልፀው በአሁኑ ሰዓት በዩኒቨርሲቲው 113 ምርምሮች እየተካሄዱ ቢሆንም የሚሰሩ ምርምሮች እና መሬት ላይ ያሉ ችግሮች ያለመጣጣም ይታያል እና የትምህርት ኮሌጅም የዚህ መሰሉን ስልጠና ከማዘጋጀት በዘለለ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመምከር ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ እና ሊፈቱ የሚገባቸውን ችግሮች በመለየት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et