የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ተደረገ

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በ2015 የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አደረገ።

 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ጥር 5 ቀን 2015 ዓ.ም በ2015 የበጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ግምገማና ውይይት አካሂዷል፡፡

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል በቀለ እንደተናገሩት ኮሌጁ ባለፉት ስድስት ወራት በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ላይ ይገኛል። ያመቱ ትምህርት በታቀደው ጊዜና ሰዓት መጀመሩን የገለፁት የኮሌጁ ዲን ለእነዚህ ተግባራት የሚረዱ ዘመናዊ የምግብ ማብሰያ በማደራጀት አገልግሎት ላይ እንዲውል መደረጉን፣ የደህንነት ካሜራ መገጠሙንና ስራ ላይ መዋሉን፣ በደን ልማት አማካኝነት ከስዊድን መንግስት ድጋፍ የተገኘ አዲስ የጣውላ መሰንጠቂያ ሥራ ጅማሮ ላይ መሆኑን እና የደን ችግኝ ጣቢያውም በዘመናዊ መልኩ እንዲደራጅ ሂደት መጀመሩን፣ ለምርምርና ለቤተ-ሙከራ አገልግሎት የሚውሉ ከ5ሚሊ. ብር በላይ የሚገመቱ ቁሳቁሶች ከአሜሪካን ኤምባሲ እንዲሁም ከ3ሚሊ. ብር በላይ የሚገመቱ ዕቃዎች ደግሞ ከኮሪያና ጀርመን መንግስታት ድጋፍ መገኘታቸውንና የትብብር ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት 8 የጋራ ስምምነት ሰነድ መፈራረሙን እንዲሁም በመውጫ ፈተና ተማሪዎች ውጤት እንዲያመጡ ፈቃደኛ በሆኑ መምህራኖች ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አክለውም በዚህ ፕሮግራምም ባለፉት ስድስት ወራት አፈፃፀማችን ላይ በመገምገምና ክፍተቶቻችን ላይ ትኩረት ሰጥተን በመወያየት በቀጣይ ወራቶች የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ በርትተን መስራት ይጠበቅብናል በማለት አሳስበዋል፡፡

በዕለቱም የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ የም/ቴ/ሽ/ም/ዲን ፅ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም የአስተዳደር ዘርፍ የስድስት ወር አፈፃፀም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀረቡትም ሰነዶች ላይ ግምገማና ውይይት በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et