የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የ2015ዓ.ም የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ግምገማ እና ውይይት በጥር 4/2015ዓ.ም አካሂዷል፡፡

የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዙፋን በደዊ በመክፈቻው ንግግራቸው ኮሌጁ ባለፉት ስድስት ወራት የተሰጡትን ተልዕኮዎችና ግቦች ለማሳካት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ የቆየ ሲሆን ይህ መድረክ  የኮሌጁን የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አዘጋጅተን ለዩኒቨርሲቲው ከማቅረባችን በፊት በኮሌጃችን የሚገኙ ትምህርት ክፍሎች በተሰጡን  ግቦች ላይ ከመማር ማስተማር፣ ከምርምርና ቴ/ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት አንጻር የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀምን በዝርዝር በማየት ክፍተቶቻችን ላይም በመመካከር በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን እንድናስቀምጥ ይረዳናል ብለዋል፡፡ አክለውም የመውጫ ፈተና ዝግጅትን በተመለከተ ለተማሪዎችና መምህራኖች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከመስጠት በዘለለ ለተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠትና ሞዴል ፈተናዎችን ማዘጋጀት፣ የቤተ-ሙከራ ቁሳቁስና መገልገያ ዕቃዎችን ማሟላትና ምቹ ማድረግ፣ ለድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠት፣  እንዲሁም ለተለያዩ ዓላማዎች የሚውል የእፅዋት አትክልት ቦታ በዩኒቨርሲቲው እየተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኮሌጁ ፕላንና መረጃ አስተዳደር አስተባባሪ አቶ ዳፋ ዱጌ በዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስር እና ከአለም አቀፍ እና በሃገር ውስጥ ከሚገኙ ተቋማት ጋር ትብብር መፍጠር ላይ በኮሌጁ ክፍተቶች እንዳሉ ጠቅሰው በቀጣይ በእነዚህ ላይ ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠበቅበት አንስተዋል፡፡

 በዕለቱም የትምህርት ክፍል  ኃላፊዎች የስድስት ወር አፈፃፀም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀረቡትም ሰነዶች ላይ ግምገማና ውይይት በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et