የስድስት ወር አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አደረገ

የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ የ2015 በጀት ዓመት የስድስት ወር አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አደረገ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅቸ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም  የ2015 በጀት ዓመት የስድስት ወር አፈፃፀም ርፖርት ላይ ውይይትና ግምገማ አደርጓል፡፡

የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ደብረወርቅ ደበበ በመክፈቻው ላይ የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ በያዝነው ዓመት ከመማር ማስተማር፣ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎቹ ጎን ለጎን በዚህ ዓመት የሚጀመረውን የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ ዝግጅት በማድረግ ለመምህራንና ተማሪዎች ፈተናውን አስመልክቶ ግንዛቤ የማስጨበጥና ተማሪዎችን ብቁ ለማድረግ፣ ዩኒቨርሲቲው እራሱን ለመቻል በሚያደርገው ጉዞም የበኩሉን ለመወጣት እንዲሁም የኮሌጁን ዓመታዊ ዕቅድ በማዘጋጀትና ተግባራዊ በማድረግ በርካታ ውጤታማ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀው የበጀት ማነስ፣ ከብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር በተያያዘ ተማሪዎች ዘግይተው መግባታቸው፣ሃገራዊ ስብሰባዎች መብዛታቸውና ፕሮግራሞች መደራረባቸው ስራዎቻችንን እንዳንሰራ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ናቸው ብለዋል፡፡ አክለውም በዛሬው ዕለትም በስድስት ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን በመወያየትና በመገምገም ባሉን ቀሪ ጊዚያቶች ሳይከናወኑ በቀሩት እና ቅድሚያ ሊሰሩ በሚገቡ አንኳር ስራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት ኃላፊነታችንን እንድንወጣ ስል አደራ እላለሁኝ ብለዋል፡፡

በዕለቱም በኮሌጁ የሚገኙ የሕግና የገቨርናንስና ልማት ጥናት ትምህርት ቤቶች፣ የስነ ዜጋና ስ/ም/ትምህርት ክፍል፣ የአካ/ጉ/ተ/ዲን እንዲሁም የም/ቴ/ሽ/ተ/ዲን የግማሽ ዓመት ሪፖርታቸውን አቅርበውና ውይይት ተካሂዶባቸው ፕሮግራሙ መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et