"የምሁራን ሚና በሃገር ግንባታ"

"የምሁራን ሚና በሃገር ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምክክር መድረክ አዘጋጀ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ "የምሁራን ሚና በሀገር ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የምሁራን የምክክር መድረክ ከታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በዋናው ግቢ እያካሄደ ይገኛል፡፡

ውይይቱ ሊካሄድ ታቅዶ የተጀመረው በሁለት ዙር ሲሆን በመጀመሪያ ዙር በዩኒቨርሲቲው አመራር አካላት እንዲሁም በሁለተኛው ዙር በመምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች መካከል እንደሚደረግ ተገልጾአል፡፡

ለመጀመሪያ ዙር ተወያዮች ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በዩኒቨርሲቲያችን የምትገኙ ከፍተኛ አመራሮችና ምሁራኖች በሀገር ግንባታ ዙሪያ ከሚቀርበው የውይይት መነሻ ሰነድ፣ ከምናውቀውና ካካበትነው ልምድ በመነሳት በምክክሩ ላይ ተሳትፏችሁን ሀገር ተፈልጋለች እና ለምክክሩ ሁላችሁም ትኩረት በመስጠት የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስና ለሀገራችን የበኩላችንን የበኩላችንን እንድንወጣ አደራ እላለሁኝ ብለዋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር እና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ክብርት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ የውይይቱን መድረክ ሲያስጀምሩ እንደሀገር ባለፉት ዓመታቶች በርካታ ችግሮችን አልፈን የተለያዩ ስኬቶችን ስንቀዳጅ በእነዚህ ጉዞዎች ውስጥ የምክክርና የውይይት አስፈላጊነትን ያየንና የተረዳን ሲሆን ሀገራችን የሁላችንም ናትና እንድንደማመጥ፣ እንድንነጋገር እንዲሁም እንድንወያይ በማለት ይህ መድረክ ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡ አክለውም ምሁራን የሀገራችንን ማህበራዊ. ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ነቅሶ በማውጣትና መፍትሄዎችን በመጠቆም እንዲሁም ጥበብና እውቀትን ከፍላጎት ጋር በማጣመር የህብረተሰብን ችግር ከመፍታትና ማህበረሰቡን ከማንቃት አኳያ ባለፉት የሀገር ግምባታ ሂደቶች ላይ ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው አውስተው  እንደሀገር በውስጣዊ ያላለቁ የፖለቲካ ችግሮች ሲኖሩ በማህበረሰቡ ውስጥም የሙስና እና የሞራል ዝቅጠት እየጎላ መምጣቱን ጠቁመው በዚህ መድረክ ችግሮቻችን ምንድናቸው ብለን መነጋገር ብቻ ሳይሆን ችግሮቻችንን ለመወጣት ‘የምሁራኑ ሚና ምንድነው? ምሁራኑስ ምን መፍትሔ አላችሁ? እንደሀገር ለማደግና ለመበልፀግ የምሁራኑ ሚና ምን መምሰል አለበት?’ የሚለውን  መወያየትና መመካከር ያለብን ሲሆን ይህም ምክክር በሀገር ደረጃ ለሚደረገው ውይይትና ለፖሊሲ ግብዓት ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ በየነ በራሳ ለውይይት መነሻ የሚሆን "በሃገር ግንባታ የምሁራን ሚና" የሚል ሰነድ ሲያቀርቡ ሀገሮች የሚመሩትና የሀገሮች ዕድገትና ብልፅግና የሚመጣው በእውቀት ሲሆን እኛም ያደጉና የበለፀጉ ሀገሮች የደረሱበት ለመድረስ የምሁራኑ ሚና የጎላ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በቀጣይም በሰነዱ መነሻ ምሁራኑ በሚነሱ ኃሳቦች ላይ ውይይትና ምክክር እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et