የሥራ አመራር ቦርድ 61ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ 61ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሄደ። የዩኒቨርሲቲው ሥ/አ/ቦርድ በዩኒቨርሲቲው ሁለንተናዊ ዕድገትና ለውጥ ላይ ያተኮረ መደበኛ ስብሰባ ታህሳስ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በዋናው ግቢ ጀምሯል፡፡

ለውይይቱ በርካታ አጀንዳዎች የቀረቡ ሲሆን ያለፈው የ60ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉባኤን ማጽደቅ እና የ2015 የሩብ ዓመት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርትን መገምገም ቀዳሚ አጀንዳዎች መሆናቸው ተገልጾአል፡፡ በተጨማሪም በውስጥ ገቢ አሰባሰብና አጠቃቀም እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ መዋቅር ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ተካሂዶ በሀገር  ደረጃ በተቀመጠው  አቅጣጫ መሰረት ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ወደመሆን የሚያድግበትን አቅም የማጎልበት እንቅስቀሴው እንዲጠናከር የሚያስችሉ ገንቢ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ ይጠበቃል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅሬታዎችን መመልከትና ተጨማሪ ከቦርዱ አባላት የሚቀርቡ ጉዳዮችንም እንደ አጀንዳ ማየት የውይይቱ አካል መሆናቸው ታውቋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et