የነጭ ሪቫን ቀን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ

 “ሴትን አከብራለሁ፤ ጥቃቷን እከላከላለሁ” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ወይም ነጭ ሪቫን ቀን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር አዘጋጅነት በደማቅ ሁኔታ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተከብሯል ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አያለ አዳቶ በዚሁ ጊዜ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ይህን ቀን ስናከብር በአከባቢያችን፣ በሠፈራችንና በሀገር አቀፍ ደረጃ በሴቶች ላይ በየትኛውም ቦታ የሚደርስባቸውን ጥቃቶች በማውገዝና በማንኛውም የሥራ መስኮች ከወንዶች  እኩል ተሳታፍና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚንደግፍበት ለዚህም ቃላችንን የሚናድስበት ቀን መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተለይም በግጭቶች ወቅት  በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች መጠነ ሰፊ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው በሀገራችን በተያያዥ ምክንያቶች የተነሳ የሴቶች የትምህርት ተሳትፎ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደነበር ጠቁመው በዪኒቨርሲቲው ደረጃ ሴቶችን በሁሉም መስኮች  እኩል ለማሳተፍ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡  

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ማኀበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር ወ/ሮ ምህረት ገነነ  በበኩላቸው በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ እየተከበረ መሆኑን ገልፀው ሴቶች በማህበረሰባችን ውስጥ በዬትኛውም ዘርፊ ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ ቢሆንም ስር በሰደዴና በተዛቡ የሥርዓተ ጾታ አመለካከቶች የተነሳ በሚፈጸሙ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ምክንያት በርካታ ሴቶች ለአካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ጥቃቶች መጋለጣቸውን አብራርተዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ስለ ነጭ ሪቫን ቀን  በዓል ታሪካዊ ዳራ በተመለከተ በዩኒቨርሲቲው የሕግ ትምህርት ቤት መምህርት ቤቴልሔም መታፈሪያ ሰፊ ገለጻ የተደረገ ሲሆን በትምህርታቸው  ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችም የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡      

 

 

    

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et