የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የ2015 ዓ.ም ሩብ ዓመት አፈፃፀም ስኬታማ መሆኑን ገለፀ።
የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ከዚህ ቀደም የመማር ማስተማሩን ሂደት የተሻለ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን ያከናወነ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ቤተመፃህፍቶቹ ዲጅታል መደረጋቸውን፣ የመኪና ጋረዥና ማጠቢያ መዘጋጀቱን፣ እንዲሁም የሰው ሃብትን በተመለከተም መረጃዎች ተሰብስበው ዲጅታላይዝ መደረጋቸውን የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ወገኔ ማርቆስ ገልፀው በያዝነው 2015 ዓ.ም ሩብ ዓመትም ግቢው ውብና ለተማሪዎች ምቹ እንዲሆን ኮሌጁ በራሱ ተነሳሽነትና ባለው ውስን ሀብት ግቢውን የማስዋብ ስራዎችን እና የተማሪዎች ምግብ ማብሰያውና ዳቦ መጋገሪያው በዘመናዊ መልኩ ግብዓቶች ተሟልተው መደራጀቱን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ወገኔ አክለውም የምግብ ማብሰያውም በዘመናዊ መልኩ መደራጀቱ የሰራተኛውን ጤና ለመጠበቅ፣ የሰራተኛውን እና የተማሪውን ጊዜ በአግባቡ ለመጠቀም እንዲሁም ከዚህ በፊት ለማብሰያ የሚባክነውን ማገዶ የሚያስቀር ሲሆን የዳቦ ማሽኑም ከኮሌጁ በተጨማሪ የአካባቢውን ማህበረሰብ ፍላጎት ለማሟላትን ለኮሌጁም ገቢ ለማግኘት ዶቦ አምርቶ ለማከፋፈል እንደሚጠቅም ተናግረዋል፡፡