ለተመራቂ ተማሪዎች  ስልጠና ተዘጋጀ

የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ በመውጫ ፈተና ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለተመራቂ ተማሪዎች አዘጋጀ።

 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን መውጫ ፈተና አስመልክቶ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም  ለዚህ ዓመት ተመራቂ የኮሌጁ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ደብረወርቅ ደበበ ከዚህ በፊት የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ ከኮሌጁ መምህራንና ኃላፊዎች ጋር የውይይትና የምክክር መድረክ የነበረን ሲሆን በዛሬው ዕለትም ለተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና ከሕግ ትምህርት ቤት ተሞክሮና ልምድ የሚቀርብበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የሕግና እና ገቨርናንስ ኮሌጅ ተባባሪ ዲን ዶ/ር ንጉስ በላይ የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ኮሌጁ የማስተባበር፣ የመደገፍና ክትትል ስራዎችን እያከናወነ እንደሆነ፣ ትምህርት ክፍሎችና መምህራኖች ኮርሶችን በመለየትና ተማሪዎችን ውጤታማ በሚያደርጉ ስራዎች ላይ ትኩረት እያደረጉ መሆኑን ጠቅሰው ተማሪዎችም በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ስለ መውጫ ፈተና ምንነትና አሰጣጥ፣ የተለዩ ኮርሶችን እንዲሁም ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቸውና መዘጋጀት እንዳለባቸው በመገንዘብ እራሳቸውን ውጤታማ ለማድረግ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

የሕግ ት/ቤት ኃላፊና መምህር በኃይሉ እሸቱ የሕግ ተማሪዎችን ላለፉት በርካታ ዓመታት የመውጫ ፈተና በማዘጋጀትና በመፈተን ት/ቤቱ ውጤታማ እንደሆነ ገልፀው ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በምን ላይ ማተኮር እንዳለባቸው፣ የስነ-ልቦና ዝግጅት በማድረግና ጭንቀትን በማስወገድ በተማሩት ትምህርት ላይ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንዲዘጋጁ አሳስበዋል፡፡

የገቨርናንስና ልማት ጥናት ት/ቤት ኃላፊና መምህር አቶ ዳኜ ጥላሁን እንዲሁም የስነምግባርና ስነ-ዜጋ ት/ክፍል ኃላፊ አቶ ተመስገን ኤልያስ በበኩላቸው ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ምንነት ተረድተውና እንዴት መዘጋጀት እንዲሁም ውጤታማ እንደሚሆኑ ገለፃ የሰጡ ሲሆን ፈተናው ከመድረሱ በፊትም አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ ለተማሪዎችን ለመደገፍ ጥረት እንደሚደረግና ሞዴል ፈተናዎችም እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ተማሪዎችም በቀረቡ ኃሳቦች ላይ የተወያዩና ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ከመድረኩም በተነሱ ጥያቁዎች ላይ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et