የወንዶ ገነት ኮሌጅ ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ዙሪያ ዉይይት ተካሄደ

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በደንና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት አካሄደ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ከባለድርሻ አካላትና ከወንዶ ገነት ከተማ ቀበሌ አስተዳደር፣ የፍትሕ አካላት፣ የኃይማኖት ተቋማትና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በሰላምና ፀጥታ እንዲሁም በደንና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ዙሪያ ህዳር 2 ቀን 2015 ዓ.ም ዉይይት አካሂዷል።

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል በቀለ በዉይይቱ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ኮሌጁ የተሰጡትን የመማር ማስተማር፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ተልዕኮዎቹን ለበርካታ አመታት በተሳካ ሁኔታ እየተወጣ ይገኛል። አክለው ሲናገሩም ኮሌጁ የአየር ንብረት ለዉጥን ለመቋቋምና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር በደንና ተፈጥሮ ሀብት ላይ እየሰራ ቢሆንም በኮሌጁና አካባቢው በሚገኘዉ ደን ላይ በህገ ወጥ ሰዎች የመቃጠልና የመመንጠር እንቅስቃሴዎች በመበራከታቸው በዚህ መድረክ በጋራ በመምከር መፍትሄ ልናበጅለት ይገባል ብለዋል።

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ በላይ በልጉዳ በበኩላቸዉ ኮሌጁ ብቻዉን ሰርቶ የታሰበዉን ዉጤት ማምጣት ስለማይቻል በዚህ መድረክ በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ፣ በዱር ህይወትና ኢኮቱሪዝም ዙሪያ፣ የደን መጨፍጨፍና ውድመትን መከላከል ላይ እንዲሁም ሰላምና ፀጥታን በተመለከተ ያሉ ተግዳሮቶችና መፍትሄዎቻቸዉ ላይ በጋራ ልንመክር ይገባናል ብለዋል።

በውይይት መድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎችም በተነሱት ርዕሶች ላይ ሰፊ ዉይይት ያደረጉ ሲሆን ተፈጥሮ የጋራችን በመሆንዋ በደንና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ላይ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች ከኮሌጁ ጋር በጋራ በባለቤትነት መስራት፥ እንዲሁም ደኑን ከቃጠሎና ጭፍጨፋ ለመከላከል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል።

የወንዶ ገነት ኮሌጅ ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ዙሪያ ዉይይት አካሄደ

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et