በመውጫ ፈተና ላይ ያተኮረ ስልጠና ተዘጋጀ

የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በመውጫ ፈተና ላይ ያተኮረ ስልጠና አዘጋጀ።

ህዳር 2 ቀን 2015 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ አካዳሚክና አስተዳደር ሰራተኞችን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች የተሳተፉበትን “Exit exam princi[ples, procedures and psychological readiness” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ላለፉት ዓመታት የሀገራችን የትምህርት ስርዓት ከጥራት ይልቅ ብዛት ላይ ትኩረት በማድረጉ በርካቶች ትምህርቱ የሚፈልገውን እውቀት ሳይገበዩ ከየትምህርት ተቋማቱ ሲመረቁ መቆየታቸውን አስታውሰው መንግስት ይህ ያስከተለውን ችግር ለመቅረፍ ተመራቂ ተማሪዎችን በሀገር አቀፍ ደረጃ የመውጫ ፈተና መስጠት አንዱ መንገድ አድርጎ ወስዷል ብለዋል። አክለውም ተማሪዎች ይህን የመውጫ ፈተና በሚወስዱበት ጊዜ ከተስተዋሉ ችግሮች መካከል ስለ መውጫ ፈተናው በቂ ግንዛቤ አለመጨበጥ እንዲሁም በጥናትና በስነልቦና አለመዘጋጀት እንደመሆኑ መጠን የዛሬው ስልጠና እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ እንደሚያግዝ ገልጸው በአካዳሚክ ስር የሚገኙ ባለሙያዎች እንደ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ አስበው መንቀሳቀስ እንደሚገባቸውና ስልጠናውም በሌሎች የዩኒቨርሲቲው ኮሌጆች ሊካሄድ እንደሚገባው ተናግረዋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዳኜ ሽብሩ በበኩላቸው ይህ ስልጠና እስከዛሬ ድረስ በነበሩት የመውጫ ፈተናዎች ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ክፍተቶችን በመገምገም እና በቀጣይ መሻሻል የሚገባቸውን ነገሮች በማካተት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ታልሞ መዘጋጀቱን አስረድተው በኮሌጁ የተማሪዎችን ዝግጁነት ለማጎልበትና የባለድርሻ አካላትን አስተዋጽኦ ለማሳደግ ስልጠናው ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወት እምነታቸውን ገልጸዋል።

በዕለቱ ስልጠናውን የሰጡት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ደርቤ ወርቅነህ እና የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህር እጩ ዶ/ር ሀብተማርያም ካሳ ስለመውጫ ፈተናው መርሆዎች እና ስለ ተማሪዎች የአእምሮ ዝግጅት ገለጻ አድርገዋል። በመሆኑም ሁሉም አካላት በጋራ በመቀናጀት መስራት እንደሚገባ የታለመውን ውጤት ለማምጣትና ዩኒቨርሲቲው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ በቁርጠኝነት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et