ማገዶ ቆጣቢ ምድጃን የማስተዋወቅ ስራዎች ተካሄደ

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃን በሀዋሳ ከተማ የማስተዋወቅ ስራዎች አካሄደ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በReREd ፕሮጀክት አማካኝነት ማገዶ ቆጣቢ ምድጃን በሀዋሳ ከተማ በተመረጡ ቦታዎች  የማስተዋወቅና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን ከህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እያከናወነ ይገኛል።

 የኮሌጁ አካዳሚክ ዲንና የReREd ፕሮጀክት ኃላፊ ዶ/ር ሽመልስ ንጋቱ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ፕሮጀክቱ ከዚህ በፊት ጥናት አድርጎና ክፍተቶችን ለይቶ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ በማምረትና ማሰራጨት ላይ ለተሰማሩ የሴት ማህበራት በንግድ ክህሎትና ምርትን የማስተዋወቅ የንድፈ ሃሳብ ስልጠና እና የተለያዩ ድጋፎችንም ማድረጉን ገልፀዋል።

ዶ/ር ሽመልስ አክለዉም ለማህበራቱ ስልጠና ከመስጠት በዘለለ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሀዋሳ ከተማ በተለምዶ አሮጌውና አዲሱ ገበያ እንዲሁም በዳቶ አካባቢዎች ከተመረጡ ሶስት ማህበራት ጋር በመሆን ተግባር ተኮር የማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎችን በተመለከተ ከኢኮኖሚያ፣ ማህበራዊ፣ ከጤና፣ ከተፈጥሮና አየር ንብረት አንፃር ያለዉን ጠቀሜታ እንዲሁም አጠቃቀሙ ዙሪያ በአማርኛና ሲዳሚኛ ቋንቋዎች የማስተዋወቅና  ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እንደሚሰሩ ገልፀዉ በቀጣይም መሰል ስራዎች የሴቶችን አቅም ለማጎልበት ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል። አንዲሁም በአካባቢው ያሉ ሴቶችም እድሉን በመጠቀም ግንዛቤያቸዉን እንዲያሳድጉና ምርቱን በተግባር እንዲገለገሉበት አሳስበዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et