የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ላይ ግምገማ ተካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2015 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ላይ ዉይይትና ግምገማ አካሄደ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2015 የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ላይ ዉይይትና ግምገማ እንዲሁም በተከለሰዉ የ2015 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም የዉይይት መድረክ ከፍቷል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ ከዚህ ቀደም የ2014 ዓ.ም አፈፃፀማችንን በመገምገም የነበሩ ክፍተቶችን  በመለየት እና በቀጣይ መስተካከል ባለባቸዉ ነጥቦች ላይ መምከር ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ በማከልም የ2015 ዓ.ም ረቂቅ ዕቅድ ላይ የተወያየን ቢሆንም ከዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኮዎቻቸው ልየታ አንጻር ዩኒቨርሲቲያችን ከዚህ ቀደም ከነበረዉ ዕቅድ በተለየ መልኩ ከአገራዊ መሪ  ዕቅድ ጋር በሚጣጣም መልኩ በተከለሰዉ የ2015 ዓ.ም ቅድ ላይ ዉይይት በሰፊው ከተወያየን በኃላ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀምንም እንገመግማለን ብለዋል።

እንዲሁም ፕሬዝዳንቱ አጽንዖት ሰጥተው ሲናገሩ ሀላፊዎች በደንብ ያዩበት ዕቅድና ሪፖርት እንዲሆን ትኩረት ተደርጎ ውይይት እንዲደረግ አሳስበው ሁሉም ኮሌጆች በተከለሰዉ ዕቅድ ላይ በመወያየት ገንቢ አስተያየታቸዉን እንዲሰጡና የተከናወኑ ተግባራትንም በጥንቃቄ በመሰነድ በአግባቡ ሪፖርት በሚያደርጉበት ሂደት ላይ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ግንዛቤ እንዲያዝ ጠንከር ያለ ሀሳብ ሰንዝረዋል፡፡ 

የዩኒቨርሲቲው የፕላንና ተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ቡርቃ የ3 ወር ሪፖርቱንና የዓመቱን ዕቅድ ሲያቀርቡ ከዩኒቨርሲቲዎች ልየታ አንጻር በሚጠበቀው ልክ በዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር ዘርፍ ከፍተኛ መሻሻል እንዲኖር በማድረግ ብቁና ተወዳዳሪ ምሩቃንን ማፍራት የተያዘው በጀት ዓመት ቁልፍ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ችግር ፈቺ ምርምሮችን ማካሄድ ብቻ ሳይሆን ውጤታማነቱንም ማላቅ ከተያዙ ዋና ዓላማዎች የሚካተት መሆኑን አቶ ሙሉጌታ አብራርተዋል፡፡

በውይይቱም ወቅት ተሳታፊ የነበሩት ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች እና የተለያዩ ሀላፊዎች በዕቅዱም ሆነ በሪፖርቱ ላይ አመርቂ ሀሳብ በመሰንዘር ትኩረት በሚሹ ዝርዝር ጉዳዮች ላይም አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ሊያጋጥሙ በሚችሉ ማነቆዎች ላይ በሰፊው መክረውበት የምክክርና የግምገማ መድረኩ አብቅቷል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et