ዘመናዊ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አምራቾች ስልጠና ተሰጠ

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ዘመናዊ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አምራቾች ስልጠና ሰጠ፡፡

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ በReREd ፕሮጀክት አማካኝነት በደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች ለሚገኙ ሴት ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አምራቾች መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም ስልጠና የሰጠ ሲሆን የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን እና የ ReREd ፕሮጀክት ኃላፊ ዶ/ር ሽመልስ ንጋቱ በሀገራችን ከምንተቀመው የኃይል ፍጆታ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው የቤት ውስጥ ፍጆታ በመሆኑ እና በባህላዊ መንገድ የምንጠቀም በመሆኑ የተጠቃሚዎችን ጤና የሚጎዳ፣ የአየር ንብረትን የሚጎዳና ብዙ እንጨት የሚፈጅ መሆኑን ገልፀው ዘመናዊ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ግን የማገዶ አጠቃቀምን እንደሚቆጥብ፣ የአየር ብክለተን እንደሚያስወግድ እና የተጠቃሚዎችን ጤና የማይጎዳ በመሆኑ ህብረተሰቡ ይሄንን ምርት እንዲጠቀም በዚህ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ሴት አምራቾች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ሽመልስ አክለውም ፕሮጀክቱ ከዚህ በፊት ዘመናዊ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ለሚያመርቱ ሴት አምራቾች በሌላ ርዕስ ስልጠና መስጠቱን አውስተው በዛሬው ዕለት በጥናት በለየናቸው ችግሮቻቸው ላይ ማለትም ንግዳቸውን የተሻለ ለማድረግ በዕቅድ አዘገጃጀት፣ በምርት ገበያ ውሳኔና ዋጋ አወጣጥ ላይ እና ምርታቸውን የማስተዋወቅ ክህሎት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሰልጣኝ ወ/ት ሃምሳለ ባረጋ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ አምራች ሲሆኑ ስልጠናውን አስመልክቶ እንደተናገሩት ዘመናዊ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ማምረት ከጀመርኩ ብዙ ዓመት ቢሆነኝም በሃገራችን ህብረተሰቡ ብዙ ያልለመደው በመሆኑ፣ የገበያ ትስስር ባለመኖሩ እና ምርቱን ለማምረት በተለይ በአሁኑ ሰዓት የግብዓት እጥረት በመኖሩ እና ቢገኝም የዋጋ ንረት መኖሩን ተናግረው ኮሌጁ ትክክለኛ ባለሙያና አምራቾችን በመለየትና የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ በመሆኑ አመስግነው መንግስትም ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ግብዓቶችን ለምሳሌ ስሚንቶና ብረት የምናገኝበት ቢያመቻችልን ብለዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et