የመማሪያ መርጃ ቁሳቁሶዎችን ለተማሪዎች ተበረከተ

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የመማሪያ መርጃ ቁሳቁሶዎችን ለተማሪዎች አበረከተ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴ/ሽግግር ም/ፕ/ ፅ/ቤ/ት ስር የሚገኘው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከኤስ ኦ ኤስ ህፃናት መንደር ፕሮግራም ሀዋሳ ጋር በመተባበር በሀዋሳ ከተማ ሁለት ት/ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች የመማሪያ መርጃ ቁሳቁሶዎችን በመስከረም 7/2015ዓ.ም አበርክቷል፡፡

አቶ ማርቆስ ፍስሐ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ተገኝተው እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማሩና ከምርምር ስራዎቹ ጎን ለጎን የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ተደራሽ ለማድረግና ማህበረሰቡን ለመደገፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በጨፌ ኮቴ ጀዌሳ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ እና ቶምቦያ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለሚገኙ 300 ተማሪዎችና ከዚህ በፊት ደጋፍ ተደርጎላቸው በተለያዩ ቦታዎች ለሚማሩ 50 ተማሪዎች በድምሩ ለ350 አቅመ ደካማ ወላጆች ላሉዋቸው ተማሪዎች ትምህርት ለመማር የሚረዳቸውን የመማሪያ መርጃ ቁሳቁሶዎችን አበርክተናል ብለዋል፡፡

አቶ ሰለሞን ያዕቆብ የኤስ ኦ ኤስ ህፃናት መንደር ፕሮግራም ሀዋሳ አስተባባሪ እንደተናገሩት ከዚህ በፊት በዚህ የጋራ ፕሮጀክት መሰል ድጋፎችና የተለያዩ ድጋፎች በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በትምህርት፣ በህይወት ክህሎት፣ በምግብ አዘገጃጀትና ማሽከርከር ክህሎት ስልጠና፣ ስለ ልጆች አስተዳደግና አያያዝ፣ የንግድና ቁጠባ ክህሎት ስልጠናዎች ለወላጆችና ወጣቶች መሰጠቱን አውስተው ከዚህ በተጨማሪም ተማሪዎችን ከመደገፍ በዘለለ ለወላጆቻቸው ልጆቻቸውን እንዲንከባከቡ የተሻሻሉና ምርት የሚሰጡ ሁለት ሁለት ፍየሎች እና የፍራፍሬ ችግኞች ድጋፍ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች ቤተሰቦችም በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን የገለፁ ሲሆን የዚህ መሰሉ ድጋፍ ላለፉት ስድስት ዓመታት መደረጉን እና ለቀጣይ ሁለት ዓመታትም እንደሚቀጥል ካገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et