በወንዶገነት የአርሶ አደሮች መስክ በዓል ተከበረ

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በወንዶገነት የአርሶ አደሮች መስክ በዓል አከበረ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴ/ሽግግር ም/ፕ/ፅ/ቤት የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ድጋፍ በመኸር የለማ የፓይነር በቆሎ ምርት በወንዶ ገነት አርሶ አደሮች ማሳ ላይ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጉብኝት ተካሂዷል፡፡

የምርምርና ቴ/ሽግግር ም/ፕ/ፅ/ቤት በማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት አማካኝነት የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በሰብል ልማት፣ በእንስሳት እርባታ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በትምህርት፣ በጤናና ስነ-ምግብ  እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች በርካታ ስራዎችን እየሰራና አርሶ አደሮችን እየደገፈ የሚገኝ ሲሆን በወንዶ ገነት አምስት ቀበሌዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች ድጋፍ ያደረጋውን በመኸር  የለማ የፓይነር በቆሎ ምርት ለባለድርሻ አካላት በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ አስጎብኝቷል፡፡

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ፍስሐ የዚህ ፕሮግራም ዓላማ በዚህ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች በመኸር ድጋፍ ያደረግንላቸውን የፓይነር በቆሎ በመዝራት የምርት ውጤቱ ምን እንደሚመስል ለባለድርሻ አካላት ለማስጎኘት፣ ከአርሶ አደሮቹም በምርት ሂደቱ ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች ለመለየት እና አርሶ አደሮቹም እርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን እንዲያሳድጉ ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም አርሶ አደር አስፋው ዘርፉ  ከዚህ በፊት ሌሎች እንደ ቀይ ሽንኩርትና ጥቅል ጎመን ያሉትን እያመረትን የቆየን ሲሆን ይህ በድጋፍ ያገኘነው የበቆሎ ዘር አዲስ ዝርያ እንደመሆኑ በተግባር ዘርተን ውጤታማ መሆኑን በመረዳታችን በቀጣይ ይህንኑ ሰፋ አድርገን ለማምረት ዕቅድ ይዘናል ብለዋል፡፡

በዕለቱም የምርምርና ቴ/ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ተገኝተው ጥሪ ከተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የአርሶ አደሮች ማሳን በመጎብኘትና ከአርሶ አደሮችም ጋር ውይይት በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et