አዲስ መዋቅር ረቂቅ ላይ ውይይት ማካሄድ ተጀመረ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው አዲስ መዋቅር ረቂቅ ላይ ውይይት ማካሄድ ጀመረ፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እንደ ሀገር የትምህርት ሚኒስቴር በተልዕኮቻቸው ዩኒቨርሲቲዎችን ሲደለድል የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብለው ከተለዩት አንዱ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ዩኒቨርሲቲዎች እንደ አዲስ የመዋቅር ለውጥ ትግበራ ላይ በመሆናቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲም በመዋቅር ረቂቁ ላይ ለመወያየት በሐምሌ 28/2014ዓ.ም የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በመክፈቻው ላይ እንደተናገሩት የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ልየታዎችን በማድረግ እንደየተሰጣቸው ተልዕኮም መዋቅሮችን በማጥናትና ከዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎች ጋርም ውይይት ያደረገ ሲሆን በድጋሚ እንድናየው እና አስተያየት እንድንሰጥበት የመዋቅር ረቂቁን የላከልን በመሆኑ ከዩኒቨርሲቲያችን የሰው ሃብትና ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ጋር በመሆን በየደረጃው ያላችሁ ኃላፊዎች በክፍላችሁ ያለውን መዋቅር በጥልቀት በመፈተሽና ተገቢውን አስተያየት በመስጠት የረቂቁን የመጨረሻ ክፍል በተሳካ ሁኔታ አዘጋጅተን በመሰነድ መላክ ይኖርብናል ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም በመጣው መመሪያ መሰረት እንደትምህርት ሁሉ ብዛት ላይ ሳይሆን ጥራት ላይ ትኩረት በማድረግ የሰው ሃይላችንን ለማደረጀት የስራ ክብደት እና ኃላፊነትን ታሳቢ በማድረግ የተሰጠንን ተልዕኮ ሊወጡ የሚችሉ ባለሙያና ፈፃሚዎችን የሚያካትት መዋቅር አዘጋጅቶ ለመሰነድ ሁሉም በኃላፊነት የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል ብለዋል፡፤

በተያዘው ፕሮግራም መሰረትም የዩኒቨርሲቲው የሰው ሃብትና ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተሰማ ዳንጉሼ መነሻ የሚሆነውን የመዋቅር ረቂቅ በማቅረብ ላይ ሲሆኑ በቀጣይም በቀረበው ረቂቅ መሰረት ጥልቅ ውይይትና አስተያየት በየደረጃው ካሉ ኃላፊዎችና ተሳታፊዎች እንደሚሰጥበት ይጠበቃል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et