በምርምር ፖሊሲ ብሪፍ አዘገጃጀት ላይ ለተመራማሪዎች ስልጠና ተሰጠ

የምርምር ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ለሁለተኛ ጊዜ በምርምር ፖሊሲ ብሪፍ አዘገጃጀት ላይ ለተመራማሪዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት በምርምር ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት አማካኝነት በዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች ከሚሰሩ  ጭብጥ ተኮር ምርምሮች የፖሊሲ ብሪፍ ለማዘጋጀት የሚረዳቸውን የፖሊሲ ብሪፍ አዘገጃጀት ስልጠና በሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ ለተመራማሪዎች ሰጥቷል፡፡

የምርምር ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ራህመቶ አበበ ስልጠናውን አስመልከተው እንደተናገሩት በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ምርምሮች የሚሰሩ ሲሆን ጭብጥ ተኮር ምርምሮች በባህሪያቸው ከተለያዩ ሙያ ዘርፎች የተውጣጡ ተመራማሪዎች በአንድ ምርምር ላይ በመሳተፍ ችግሮቹን እንደየሙያቸው ከተለያዩ አቅጣጫዎች በመመልከትና በመፈተሽ ለችግሩም መፍትሔ የሚፈልጉበት የምርምር አይነት በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ከምርምር ውጤቶቹ በርካታ ነገሮችን ይጠብቃል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም ተመራማሪውም የምርምር ውጤቶችን የማሳተም፣ ጉባኤ፣ ሴሚናር እና የጥናት አውደ-ራዕይ በማዘጋጀት ለባለድርሻ አካላት ማቅረብ እና የምርምሩን ውጤትም ለተጠቃሚው ማስተላለፍ ያለበት ሲሆን ከሚጠበቁ የምርምር ውጤቶች ዋነኛው እና አንዱ የፖሊሲ ብሪፍ በማዘጋጀት ለመንግስት አካላት ማቅረብ መሆኑን ገልፀው የፖሊሲ ብሪፍ የተለመዱ አሰራሮችን፣ መመራያዎችን እና ዘዴዎችን ሊያስቀር የሚችልና በውጤቱ መሰረትም ሌላ አቅጣጫ በማሳየት ነባሩን ሊተካ የሚችል በመሆኑ እንዲሁም የምርምር ውጤቶች ደግሞ ሁልጊዜም አዳዲስ በመሆናቸው አዳዲስ ዘዴዎችን ለማሳያት የፖሊሲ ብሪፍ ማዘጋጀት አሰፈላጊ መሆኑ ታምኖበት በዚህ ላይ ልምድ ባላቸው ምሁራን ከዚህ በፊት ለተመራማሪዎቻችን ስልጠና የሰጠን ሲሆን በዛሬው ዕለትም ሁለተኛውን ስልጠና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲና ልማት ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፕ/ር ተስፋዬ ሰመላ ስልጠናው እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et