በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ስር ለሚገኙ ስራ ኃላፊዎች የሶፍትዌር ግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች አገልግሎት እንዲሁም በቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ስር ለሚገኙ ስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በከፍትኛ ትምህርት መረጃ ስርዓት አስተዳደር (HEMIS) ሶፍትዌር ላይ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና በሰኔ 9 ቀን 2014 ዓ.ም ተሰጥቷል፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕላንና ተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙልጌታ ቡርቃ ስልጠናውን አስመልክተው ከዚህ በፊት የትምህርት ሚኒስቴር በከፍትኛ ትምህርት መረጃ ስርዓት አስተዳደር (HEMIS) ሶፍትዌር ላይ በዩኒቨርሲቲያችን ለሚገኙት የፕላንና ተቋማዊ ለውጥ እና የአይ ኤስ ቲ ዳይሬክቶሬት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት በቀጣይ ይህ ሶፍትዌር በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተግባራዊ እንዲሆን አቅጣጫ ያስቀመጠ በመሆኑ እኛም በዛሬው ዕለት ስለ ሶፍትዌሩ አተገባበርና አጠቃቀም በዩኒቨርሲቲያችን ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ስር ለሚገኙ ኃላፊዎችና ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንዲያገኙ ያደረግን ሲሆን ከዚህም ጋር ተያይዞ በቀጣይ ዓመት ዕቅድ አዘገጃጀትም ላይ ውይይትና ምክክር አድርገናል ብለዋል፡፡
የአይ ኤስ ቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እሱባለው ገ/ማርያም በበኩላቸው የሶፍትዌሩን ጠቀሜታ አስመልክተው እንደገልፁት ሶፍትውሩ የመረጃ ልውውጥ ግልፀኝነትን እና ተጠያቂነትን ያለው እንዲሆን፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ለማዘመን፣ የመረጃ ጥራትን ለመጨመር፣ ተደራሽና ዘላቂ ለማድረግ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ለሚሰራቸው የመማር ማስተማር፣ ለምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በርካታ መረጃዎችን የሚይዝ በመሆኑ እንደ ግብዓት እንዲጠቀምባቸው የሚያስችል ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ሰልጣኞችም የዚህ መሰሉ ስልጠና መረጃን በተፈለገው ጊዜና ቦታ ለማድረስና ለመቀበል እንዲሁም አስፈላጊ በሆነ ጊዜም እንደ ግብዓት ለመጠቀም የሚያስችል መሆኑን እና የመረጃ ፍሰቱን እንደሚያዘምን ገልፀው መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና ሁሉም ባለሙያዎች ስልጠናውን እንዲወስዱ ተደርጎ ተግባራዊ እንዲሆን አስተያየታቸውን ተናግረዋል፡፡