በአርሶ አደሮች ማሳ እየተሰራ ያለውን ጥምር ግብርና ምልከታ ተደረገ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአርሶ አደሮች ማሳ እየተሰራ ያለውን ጥምር ግብርና ምልከታ አደረገ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የዓሳ እርባታ ምርምርና ትምህርት ማዕከል በሲዳማ ክልል ዳሌ ወረዳ እና በይርጋለም ከተማ አስተዳዳር በአርሶ አደሮች ማሳ እየተሰራ ያለውን የዓሳ፣ ዶሮ እና የጓሮ አትክልት ጥምር ግብርና በሰኔ 2/2014ዓ.ም ምልከታ አደረገ፡፡

ዶ/ር ካሳዬ ባልከው የዓሳ እርባታ ምርምርና ትምህርት ማዕከል ኃላፊ እንደተናገሩት ባለፉት ዓመታት ጥምር ግብርናን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው በሲዳማ እና አጎራባች ክልሎች ለሚገኙ ከ450 በላይ አርሶ አደሮች በዶሮ፣ በጓሮ አትክልትና በዓሳ እርባታና መረብ አዘገጃጀት ላይ የተለያዩ ስልጠናዎች ከመስጠታችን በተጨማሪ ከክልል እና ወረዳዎች የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ፅ/ቤት ጋር በመሆን በተግባር በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ በመገኘት የማሳ አዘገጃጀትና የዓሳ ማምረቻ የሚሆን ገንዳ አዘገጃጀት ላይ የማማከርና የግብዓት አቅርቦት የማድረግ እንዲሁም ከ115 ሺህ በላይ የአሳ ጫጩቶችን በማከፋፈል ድጋፍና ክትትል ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለትም እስካሁን ሲደረግ የነበረውን ሂደትና ውጤት በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትና ከፍተኛ ኃላፊዎች ተገኝተው በመጎብኘት በቀጣይ መደረግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ለመምከር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር አያኖ በራሶ ጉብኝቱ ከተደረገ በኃላ እንደገለፁት ይህ የዓሳ፣ ዶሮ እና የጓሮ አትክልት ጥምር ግብርና እርስ በርሱ ተመጋጋቢ እና ውጤታማ ሲሆን አርሶ አደሮች እና ወጣት ስራ አጦች በዘርፉ በመሳተፍ እና ጠንክረው በመስራት ምርትና ምርታማነትን መጨመር ቢችሉ የገብያ እድሉ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው በተለይ በዓሳ እርባታ ላይ ትኩረት በመስጠት ዓሳውን አምርቶ ከመሸጥ ይልቅ ወደ ምግብነት ተለውጦ ለተመጋቢና ሸማቾች ቢቀርብ አዋጭነቱ ከፍተኛ እንደሆነ በመግለፅ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም በዓሳ መረብ አሰራርና በዓሳና ዶሮ መኖ አዘገጃጀት ላይ ተጨማሪ ስልጠናዎችን እና ድጋፎችን እንደሚያደርግ እንዲሁም በይርጋለም ለሚገኙ ሳምራ የዓሳና አትክልት ማህበር ወጣት ስራ ፈጣሪዎች  በርትተው ሰርተው ውጤታማ መሆን ከቻሉ ለአባላቱ ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ዕድል እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት አርሶ አደሮችና ወጣት ስራ ፈጣሪዎቹ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ላደረገላቸው እገዛ አመስግነው በቀጣይ የተመረጡ የጓሮ አትክልት ምርጥ ዘሮችን እና የአሳ ጫጩት ዝርያ አይነቶችን እንዲያቀርብላቸው እና በመረብ እና መኖ አዘገጃጀት ላይ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እንዲያመቻችላቸው እንዲሁም ምርቱ እየጨመረ ሲመጣ የዕሴት ሰንሰለቱን በማስተሳሰር ለገብያ ተደራሽ የሚሆንበትን መንገድ እንዲፈጠርላቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et