በምግብ አያያዝና ንፅህና ላይ ስልጠና ተሰጠ

የቴክኖሎጂ ሽግግርና የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት በምግብ አያያዝና ንፅህና ላይ ስልጠና ሰጠ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት ከጂ አይ ዜድ ጋር በመተባበር ከሲዳማ ክልል ይርጋለም እና ሎካ አባያ ለተውጣጡ ወጣቶች በምግብ አያያዝና ንፅህና ላይ ከግንቦት 11-13/2014 ዓ.ም ድረስ በአዋዳ ካምፓስ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

አሰልጣኝ ተሻለ በሱፍቃድ በሀዋሳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የምግብ ሳይንስ መምህር እንደገለፁት ስልጠናው ምግብን በተመለከተ ከእርሻ አንስቶ አስከ ጉርሻ ድረስ ያለውን ሂደት ያካተተና በምግብ አያያዝ፣ ንፅህናና ደህንነት ዙሪያ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ምግብ ምን ማለት እንደሆነ፣ ምግብ ሲዘጋጅ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ምግብ የሚያዘጋጁ ባለሙያዎች እንዴት ንፅህናቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው፣ ምግብ በውስጡ የያዘውን ንጥረ ነገር እንዳያጣ በምን ያህል የሙቀት መጠን መብሰል እንዳለበት፣ ምግብ ከተዘጋጀ በኃላ ሳይበላሽ ሳይበላሽ እንዴት መቆየት እንደሚቻል፣ በንክኪ የሚመጡ በሽታዎችን እና የተመጋቢውን ጤና በማይጎዳ መልኩ ተዘጋጅቶ ለተጠቃሚው መድረስ እንዳለበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልፀው ወጣቶቹ በልምድ የሚሰራውን አሰራር በመተው ሣይንሱ በመከተል እንዲሰሩ የሚያስችል ስልጠና በመሆኑ በዘርፉ ውጤታማ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡

ስልጣኞችም ባገኙት ስልጠና መደሰታቸውን ገልፀው የዚህ መሰሉ ስልጠና በዘርፉ ያለንን እውቀት የሚያሰፋልን ሲሆን የምንሰራውንም ስራ ጠንቅቀን በማወቅ ለመስራት ይረዳናል ብለዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et