በቤተ-ሙከራ አያያዝና አጠቃቀም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በቤተ-ሙከራ አያያዝና አጠቃቀም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በቤተ-ሙከራ አያያዝና አጠቃቀም ላይ ለቴክኒካል ባለሙያዎችና ለቤተ-ሙከራ ተቆጣጣሪዎች ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የአካዳሚክ ጉዳዮች ተባባሪ ዲን ዶ/ር ይፋት ደንባርጋ በኮሌጃችን በንድፈ-ሃሳብ የሚሰጡ ትምህርቶች ውጤታማ እንዲሆኑ በተግባር ትምህርትና ምርምሮች በቤተ-ሙከራዎች ስለሚደጉፉ በተቀናጀ መልኩ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማስቀጠል እና ውጤታማ የሆነ የተማረ የሰው ኃይል ለማፍራት በዛሬው ዕለት ለቴክኒካል ባለሙያዎችና ለቤተ-ሙከራ ተቆጣጣሪዎች በቤተ-ሙከራ አያያዝ፣ አጠቃቀም፣ ስለመሳሪያዎች አያያዝና አጠቃቀም እንዲሁም በቤተ-ሙከራ ሊተገበሩ ስለሚገባቸው የደህንነት አሰራሮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ይፋት አክለውም ከዚሁ ጋር በተያያዘም የቤተ-ሙከራ ዕቃዎች በዕዳትና በጥንቃቄ እንዴት መያዝ እንዳለባቸው እና ሲበላሹሙ በቀላሉ እንዴት ተጠግነው ስራ ላይ እንደሚውሉ በተግባር ስልጠናው እየተሰጠ ሲሆን ከዚህ ስልጠና ባለሙያዎች ባገኙት ክህሎት በቤተ-ሙከራ የሚሰጡት አገልግሎቶችን ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ ዕቃዎቹም በሚፈለገው ደረጃ ለሚፈለገው ዓላማ በማዋል ረጅም ጊዜ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ለማድረግ ስልጠናው እንደሚረዳቸው ገልፀዋል፡፡

በስልጠናውም ላይ 52 ሰልጣኞች ስልጠናውን የተካፈሉ  ሲሆን የዚህ መሰሉ ስልጠና አስፈላጊ መሆኑን እና አዳዲስ የቤተ-ሙከራ ዕቃዎች ሲመጡም መሰል ስልጠናዎች መሰጠት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et