በወተት ላሞች የግት በሽታ እና እንክብካቤ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

የእንስሳት ሕክምና ፋካሊቲ በወተት ላሞች የግት በሽታ እና እንክብካቤ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና ፋካሊቲ ከማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በወተት ላሞች የግት በሽታ እና እንክብካቤ ዙሪያ ለወተት ለእንስሳት ጤና ቴክንሺያኖች ከግንቦት10-11 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የግንዛቤና ክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የእንስሳት ሕክምና ፋካሊቲ ዲን ዶ/ር አመነ ፈቃዱ በመክፈቻው ላይ እንደተናገሩት በሀገራችን ከፍተኛ የከብቶች ቁጥር ቢኖርም ከእንስሳው የሚገኘው ጥቅም ወተትን ጨምሮ እጅግ አናሳ ሲሆን ለእዚህም እንደምክንያት የሚጠቀሱ በርካታ ተግዳሮቶች ሲኖሩ የወተት ምርትን ከሚቀንሱት ውስጥ በላሞች ግት ላይ የሚከሰቱ በሽታዎች ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልፀው ሰልጣኞች በዚህ ስልጠና ስለበሽታውና መከላከያ ዘዴዎቹ የሚያገኙትን ክህሎት ከራሳቸው ልምድና ተሞክሮ ጋር በማዋሃድ የመፍትሄው አካል በመሆን እና የወተት ምርታማነትን በማሳደግም ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

በእንስሳት ሕክምና ፋካሊቲ የባዮሜዲካል ሳይንስና ማይክሮ ባዮሎጂ ዶ/ር ነብዩ ሞጄ ባለፉት 10 ዓመታት በዘርፉ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከላሞች ግት በሽታ ጋር የተያያዙ ችግሮች መከሰታቸውን የሚያሳዩ በመሆኑ ይሄንን ችግር ለመቀነስና ለመከላከልም ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው በዚህ ስልጠናም የጡት በሽታ ምን ማለት እንደሆነ፣ መንስኤዎቹን፣ የመተላለፊያ መንገዶቹን፣ ምልክቶቹን፣ የምርመራና ልየታ ሂደቶችን እንዲሁም የመከላከያ ዘዴዎቹን በንድፈ- ሃሳብና በተግባር የተደገፈ ስልጠና ለከብት አርቢዎችና ለእንስሳት ጤና ቴክንሺያኖች የተሰጠ ሲሆን ከሰልጣኞችም በዘርፉ ያጋጠማቸውን ተግዳሮቶችና የተወሰዱ መፍትሄዎችን የልምድ ልውውጥ የተደረገበት መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎች እና አሰልጣኞች ከሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲው ባለድርሻ አካላት ጋር በስልጠናው ዙሪያ እና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጥባቸው ስለሚገባቸው ተያያዥ ርዕሶች እንዲሁም በጋራ ቢሰሩ ውጤታማ ይሆናሉ ባሉዋቸው ነጥቦች ላይ የጋራ ውይይት አድርገው ስልጠናው የተጠናቀቀ ሲሆን ከአርሲ ነገሌ፣ ሻሸመኔ፣ ከሀዋሳ እና ይርጋለም በድምሩ 33 የእንስሳት ጤና ቴክንሺያኖችና 50 ከብት አርቢዎች በስልጠናው መሳተፋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et